Your browser doesn’t support HTML5
የሶማሊያና የኢትዮጵያ ግንኙነት በታሪክ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያለፈ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እአአ በ1964 እና በ1977 በግዛት ይገባኛል በተነሳ ውዝግብ ሳቢያ በተለያዩ ሁለት ጊዜያቶች የተዋጉት ሁለቱ ጎረቤት ሃገራት ግንኙታቸው ሁልጊዜም ታዲያ ቀዝቃዛ አልነበረም፡፡
SEE ALSO: ስምምነቱን የተቃወመችው ሶማሊያ አምባሳደሯን ጠራችይሁን እንጂ ባለፈው የታኅሳስ ወር ኢትዮጵያ ከሶማሌ ተገንጥላ ራሷን ነጻ ግዛት ብላ ከሰየመችው ሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ግንኙነታቸውን ዳግም ከብርቱ ፈተና ላይ ሊጥለው በቅቷል፡፡