አቶ ሃብታሙ አያሌው የህክምና እርዳታ ሲያገኘበት ከቆየበት ሆስፒታል ወደ ሌላ ቦታ ተዛወረ

  • መለስካቸው አምሃ

አቶ ሃምታሙ አያሌው

የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ የነበረው አቶ ሃብታሙ አያሌው የህክምና እርዳታ ሲያገኝበት ከቆየበት ሆስፒታል ዛሬ ወደ ሌላ ስፍራ ለመዛወር መገደዱ ታወቀ።

አቶ ሃብታሙ አያሌው ወደ ውጭ አገር ሄዶ ለመታከም የሚያስፈልገውን መረጃ የማሟላት ጥረቱ እንደቀጠለ መሆኑን የቅርብ ምንጮች ገለጹ።

አቶ ሃብታሙ አያሌው ባጋጠመው ህመም ራሱን ስቶ ካዲስቶ እየተባለ ወደ ሚጠራው ሆስፒታል ገብቶ እስከዛሬ ድረስ የህክምና አገልግሎት ሲሰጠው የቆየ ቢሆንም ከዛሬ በኋላ ሊቀጥል እንደማይችል ሆስፒታሉ ገልጾለታል። አቶ ሃብታሙ አያሌውን በቅርብ ከሚከታተሉት ወዳጆቹ አንዱ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ሆስፒታሉ ወደዚህ ውሳኔ የደረሰው ተገቢውን ህክምና መስጠት ባለመቻሉ መሆኑ ነው።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

አቶ ሃብታሙ አያሌው የህክምና እርዳታ ሲያገኘበት ከቆየበት ሆስፒታል ወደ ሌላ ቦታ ተዛወረ