“የአምስት ቀን አራስ ልጄን እንደያዝኩ ጥዬ ሸሽቻልሁ” አንዲት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪ

ቤት መፍረሱን የተቃወሙ ነዋሪዎች በአዲስ አበባ መስተዳድር ሴቶችና ሕፃናት ቢሮ አቤቱታ ሲያቀርቡ

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለመዶ ሀና ማርያም፣ ፉሪ፣ ቀርሳ፣ ኮንቱማ እና ማንጎ ጨፌ በተባሉ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤታቸው በዶዘር እየፈረሰና ወንዶች በአካባቢው እንዳይጠጉ መከልከሉን ነዋሪዎች ተናገሩ።

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለመዶ ሀና ማርያም፣ ፉሪ፣ ቀርሳ፣ ኮንቱማ እና ማንጎ ጨፌ በተባሉ አካባቢዎች ዕረቡ ዕለት ከቤት መፍረስ ጋር በተያያዘ በአካባቢው ነዋሪዎችና በፖሊስ መካከል በተነሳ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወሳል። የአካባቢው ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤቶቹ ከትናንት ጀምሮ በዶዘር እየፈረሰባቸው እደሆነና ወንዶች ወደ አካባቢው እንዳይገቡ እንደተከለከሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ማምሻውን ነዋሪዎቹን አነጋግሯል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

“የአምስት ቀን አራስ ልጄን እንደያዝኩ ጥዬ ሸሽቻልሁ” አንዲት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪ