የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት የግዴታ ምልመላ ያካሂዳሉ ላለው የሮይተርስ ዘገባ ምላሽ ሰጡ

መቀሌ

መቀሌ

የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት ተዋጊዎችን በግዴታ እየመለመሉ ነው በሚል በሮይተርስ የዜና ወኪል የቀረበውን ዘገባ የትግራይ ክልል የውጭ ግኑኝነት ጽሕፈት ቤት የተቀናጀ ዘመቻ ሲል በመኮነን ምላሽ ሰጥቷል።

ጽህፈት ቤቱ በሰጠው ምላሽ የትግራይ ህዝብና ወጣቶች ሮይተርስ እንዳለው ሳይሆን "ወራሪ ኃይል" ሲል የጠራውን ለመከላከል በፈቃዳቸው የታጠቁ ናቸው። መኮነን ካለበት ወራሪው ብሎ የጠራው ኃይል መሆን አለበት ብሏል።

ጥቂትና በተናጠል ያጋጠሙ ክስተቶትችን ሁሉን እንደሚወክል አድርጎ ማቅረብ አይገባም ያለው መግለጫው ሮይተርስ መረጃ ለመሰብሰብ የተጠቀመበት ዘዴም ክፍተት አለው ብሏል።

በጦርነት በደቀቀችው ትግራይ ክልል ያሉ ባለሥልጣናት ወጣቶች ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር እየተካሄደ ባለው ጦርነት አንዲሳተፉ ለማስገደድ ቤተሰቦቻቸውን እያስፈራሩና እያሰሩ እንደሚገኙ ተይዘው የነበሩ ተዋጊዎች እንዲሁም ነዋሪዎች መናገራቸውን ሮይተርስ መዘገቡ ይታወሳል።