ኢትዮጵያ አዲስ ፕሬዝዳንት ሰየመች

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ አዲስ ፕሬዝዳንት ሰየመች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ስድስተኛው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል

ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም. በተካሄደው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ አዲሱን ኃላፊነታቸውን የተቀበሉት አምባሳደር ታዬ ፣ ከተሰናባቿ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር የስልጣን ርክክብ አድርገዋል።

አዲሱ ፕሬዝደንት ከስልጣን ርክክቡ በኋላ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር የጀመሩት፣ ኢትዮጵያ ያለችበትን የሰላም ዕጦት ቀውስ በማንፀባረቅ ነው፡፡ መንግሥት ከማንኛውም አካል ጋራ ለሰላም ንግግር ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሆኖም ግን “የኃይል አማራጭን በሚጠቀሙ አካላት ላይ ከዚህ በኋላ የመንግሥት ልበ ሰፊነት እጅግ የጠበበ ነው” ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህን ንግግር ያደረጉት በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሰው የፋኖ ታጣቂ ኀይል ላይ መንግሥት የተጠናከረ እርምጃ መጀመሩን ከገለፀ ከቀናት በኋላ ነው፡፡