37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ሲጀመር፣ የሶማሊያ ፕሬዝደንት “የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ወደ ስብሰባው እንዳልገባ ሙከራ አድርገዋል” ሲሉ ከሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ለፕሬዝደንቱ ክስ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
የኅብረቱ የዘንድሮ መሪ ቃል በትምሕርት ላይ ያተኮረ ቢሆንም፣ ሰላምና ፀጥታን ጨምሮ የአህጉሪቱ ያለመረጋጋት ምንጭ የሆኑ ቀውሶች ዋነኛ መነጋገሪያ እንደሚሆኑ የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር አስታውቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ደግሞ፣ በአኅጉሪቱ እድገት ላይ በማተኮር ተናግረዋል፡፡