የትግራይ የጦር አካል ጉዳተኞች ዛሬም በቂ ድጋፍ ጥየቃ ሰልፍ ወጡ

Your browser doesn’t support HTML5

የትግራይ የጦር አካል ጉዳተኞች ዛሬም በቂ ድጋፍ ጥየቃ ሰልፍ ወጡ

በአመራሮቻቸው መዘንጋታቸውን እና በቂ የሕክምና ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው ገልፀው ተቃውሞ ያሰሙ፣ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊ አባላት ዛሬ ኀሙስ በመቐለ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።

የህወሓት እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች፣ ኅብረተሰቡ ለሚያነሣቸው ጥያቄዎች ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ ሁለት ወራትን በስብሰባ ማሳለፋቸውን ሰልፈኞቹ ተችተዋል።

SEE ALSO: የትግራይ ኃይሎች የጦር አካል ጉዳተኞች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ከ41 ቀናት በላይ ያካሔደው ህወሓት፣ ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፣ ስብሰባው ረዥም ቀናት መውሰዱን ጠቅሶ ይቅርታ ጠይቋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።