እስራኤል በጋዛ ለሚደረገው ግዙፍ ጥቃት ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሆነች አስታወቀች

ጋዛ ጥቅምት 2016

የእስራኤል የመከላከያ ኃይል፤ አለም አቀፍ ቃል አቀባይ፤ ጋዜጠኞች እና ሁሉም ሰው ከጋዛ የሚወጡ የዜና መረጃዎችን ተዓማኒነት እንዲመርመር አሳሰቡ። ኮለኔል ጆናታን ኮኒሪከስ ዛሬ ዕሁድ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል። ኮለኔሉ በመግለጫቸው በደቡባዊ ጋዛ ሳላህ አል ዲን በተሰኘው እና ሰሜን ጋዛን ከደቡብ የሚያገናኘው አውራጎዳና በመያዝ ከተማ ለቀው በሚገኙ የፍልስጤም ዜጎች መኪና ላይ፤ እስራኤል የፍንዳታ ጥቃት አድርሳለች የሚለውን ቪዲዮ ያሳዩ ሲሆን፤ እስራኤል ዜጎች ያንን ስፍራ ለቀው እንዲወጡ ደጋግማ ከመጠየቅ ውጭ ጥቃት አልፈጸመችም ሲሉ ተናግረዋል።

የብርታኒያ የዜና አውታር የሆነው ቢቢሲ ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመ ባያረጋግጥም እስራኤል አለመሆኑኗን ግን አርብ ዕለት አስታውቋል።

በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀማስ በእስራኤል ላይ በፈጸመው ጥቃት 29 አሜሪካውያን ህይወታቸው ማለፉን አስታውቋል። የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ትላንት ቅዳሜ፤ እስካሁን ድረስ በጋዛ ሐማስ 120 የሚደርሱ ሲቪል ዜጎችን እንዳገተ ይገኛል ሲል አስታውቋል።

ዋሽንግተን ከግብጽ እስራኤል እና ኳታር ጋር በመሆን ፍልስጤም አሜሪካዊያን የራፋህ ድንበር እንዲሻገሩ እየሰራች ነው በማለት የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል። ጥምር ዜግነት ያላቸው ፍልስጤም አሜሪካዊያን ቁጥር 500 እንደሚደርስ ተገልጿል። የሐማስ ጽኑ ጠላት የሆኑት የግብጹ ፕሬዘዳንት አል ሲሲ ይኸን መሰል የብዙሃን መፈናቀል የፍልስጤም ሀገር የመሆን ፍላጎት ማብቂያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ግብጽ የፍልስጤም ስደተኞች በሲናይ ተራራ ዙሪያ እንዲያርፉ ተጠይቃ እምቢኝ ያለች ሲሆን፤ በሌላ በኩል እጅግ ብዙ ሀገራት ዜጎቻቸውን በግብጽ በኩል የማስወጣት ፍላጎት ስላላቸው የአንድ ሀገር ዜጎችን ከሌሎች ላበላልጥ አልችል በማለት ለዩናይትድ ስቴትስ ምላሽ ሰጥታለች።

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስት አንተኒ ብሊንከን የእስራኤል ሐማስ ጦርነት እንዳይስፋፋ በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ሚኒስትሩ ከሳውዲ ዐረቢያው የዘውድ ልዑል ቢን ሰልማን ጋር የተገናኙ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ወደ ግብጽ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ከፍልስጤም ብሔራዊ ፕሬዘዳንት ሞሃሙድ አባስ ጋር በጋዛ አፋጣኝ የሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያሻ መነጋገራቸውን ዋይት ኃውስ አስታውቋል።