በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልስጤማውያን የጋዛ ከተማን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው


ፍልስጤማውያን ጋዛን ለቀው በመውጣት ላይ (ፎቶ ኤፒ ጥቅምት 14፣ 2023)
ፍልስጤማውያን ጋዛን ለቀው በመውጣት ላይ (ፎቶ ኤፒ ጥቅምት 14፣ 2023)

እስራኤል በምድር ጥቃት ትፈጽማለች ተብሎ በሚጠበቅበት በዚህ ወቅት፣ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ዛሬ የጋዛ ከተማን ለቀው በመውጣት ላይ መሆናቸው ታውቋል።

እስራኤል የሐማስን ይዞታና አቅም ለማውደም የጋዛ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች፡፡

በጋዛ የውሃ አቅርቦቱ እያለቀ መሆኑን ያስጠነቀቁት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ጋዛን ለቀው እንዲወጡ መጠየቅ አደገኛ እና የማይቻል ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ግጭቱን ለማርገብ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በማድረግ ላይ ያሉትና፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ሰባት ሀገራትን በመጎብኘት ላይ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ዛሬ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ተገኝተው፣ የክርስትና የእስልምናና የአይሁድ የእምነት ሥፍራዎች በአንድ ላይ የሚገኝበትን ግቢ ጎብኝተዋል።

“በጨለማ ውስጥ የሚገኝ ብርሃን” ሲሉ ብሊንከን በግድግዳው ላይ መልዕክታቸውን አኑረዋል።

ብሊንከን ቀደም ብለው ሳዑዲ ዓረቢያ ጎራ ብለው የነበረ ሲሆን፣ ከሃገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሳል ቢን ፋርሃን ጋር ተገናኝተዋል።

“በማንኛውም ሰዓት እና ግዜ፣ በማንም ይሁን፣ ሲቪሎችን ኢላማ ያደርገ ጥቃት መወገዝ ይገባዋል” ሲሉ ልዑሉ መናገራቸው ተዘግቧል።

///

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG