በሊቢያ ተከስቶ የነበረው እና በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ጎርፍ፣ ከ43 ሺሕ በላይ ዜጎች ማፈናቀሉን የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰት ድርጅት (IOM) አስታውቋል።
ከአስር ቀናት በፊት "ዳንኤል" የተሰኘ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ፣ ሁለት ያረጁ ግድቦችን ሲያፈርስ የደረሰው የጎርፍ አደጋ መንደሮችን አጥቦ ሲወስድ በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል።
እስከ አሁን ከ3 ሺሕ 300 በላይ ሰዎች እንደሞቱ ይገመታል። አለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች የሟቾቹን ቁጥር ከ 10 ሺሕ በላይ ያደርሱታል።
SEE ALSO: በሊቢያ ጎርፍ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት አጠፋየመጠጥ ውሃ አለመኖር በርካቶች እንዲፈናቀሉ ማድረጉን አይኦኤም አስታውቋል። የምግብ፣ የመጠጥ ውሃ እና የሥነ አዕምሮ ምክር ዕርዳታ በአስቸኳይ እንደሚያስፈልግም ድርጅቱ አስታውቋል።
በጦርነት የተደቆሰችው ሊቢያ፣ በምዕራብ በተመድ የሚደገፈው ጊዜያዊ መንግሥት እና፣ በአደጋ በተመታችው ምሥራቅ ደግሞ በካሊፋ አፍታር በሚመራው ኃይል ተከፍላለች፡፡