በፍኖተ ሰላሙ ጥቃት ውዶቻቸውን ያጡ የከተማዋ ነዋሪዎች በቁጣ እና ቁጭት ውስጥ እንደኾኑ ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

በፍኖተ ሰላሙ ጥቃት ውዶቻቸውን ያጡ የከተማዋ ነዋሪዎች በቁጣ እና ቁጭት ውስጥ እንደኾኑ ገለፁ

ባለፈው እሑድ በተፈጸመ የከባድ መሣሪያ ጥቃት በርካታ ነዋሪዎቿን ያጣችው፣ በዐማራ ክልል የምዕራብ ጎጃም ዞን ከተማ - ፍኖተ ሰላም፣ ዛሬ መጠነኛ መረጋጋት ቢታይባትም፣ በደረሰው ሰብአዊ ጉዳት፣ ቁጣ እና ቁጭት እንዳሳደረባቸው፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

በጥቃቱ ቆስለው በሕክምና ላይ ከሚገኙ ነዋሪዎች፣ ከጉዳታቸው የተነሣ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን፣ በዛሬው ዕለትም ከሆስፒታል ሲወጣ እንደተመለከቱ፣ አክለው ተናግረዋል።

SEE ALSO: በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ በተፈጸመ ጥቃት 26 ሰዎች እንደተገደሉ ተገለጸ

በተመሳሳይ፣ ከፍኖተ ሰላም ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው የቡሬ ከተማም፣ ትላንት ከቀትር በኋላ እና ዛሬ፣ አንጻራዊ ሰላም በመገኘቱ፣ የሞቱ ሰዎችን እየቀበሩ እንደኾነ፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል። ወደ ሁለቱም ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጸጥታ ኃይል እንደገባም ጠቁመዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።