የዋጋ ንረቱን መቋቋም የተሳናቸው ነዋሪዎች

Your browser doesn’t support HTML5

የዋጋ ንረቱን መቋቋም የተሳናቸው ነዋሪዎች

የኑሮ ውድነት፣ ከቀን ወደ ቀን ፈተና እየኾነባቸው እንደሚገኝ፣ በዐዲስ አበባ ከተማ፣ አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ መንግሥት፣ የዋጋ ንረቱን ሊያቃልሉ የሚችሉ ርምጃዎችን እንዲወስድም ተማፅነዋል፡፡

የዋጋ ንረት፣ የመላው ዓለም ፈተና እንደኾነ፣ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የገለጹት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ንረት፣ መጠነኛ መሻሻል ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡

SEE ALSO: የዋጋ ንረት እየፈተነው ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ

መንግሥት፣ የቀጣዩን ዓመት በጀት ያዘጋጀው፣ የዋጋ ንረትን ሊቀንስ በሚችል መንገድ እንደኾነም አብራርተዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ የምጣኔ ሀብት ባለሞያ እና ተንታኝ ዶር. ቆስጠንጢኖስ በርሄ ግን፣ መንግሥት በገበያው ላይ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን ከመቀነስ ጀምሮ፣ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር መውሰድ ያለበትን ርምጃ ጠቁመዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።