በሰሜን ምዕራብ ናጄሪያ መስጂድ ውስጥ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ

የናይጄሪያ ወታደሮች በዛምፋራ ግዛት

የናይጄሪያ ወታደሮች በዛምፋራ ግዛት

በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ዛምፋራ ግዛት መስጂድ ውስጥ ታጣቂ ወንዶች ባደረሱት ጥቃት 15 ሰዎች መገደላቸውን ሦስት የአካባቢው ነዋሪዎች ትላንት ቅዳሜ ለሮይተርስ አስታወቁ።

በባኩዩም አካባቢ በሩማ ጊጀማ በተሰኘው አካባቢ በደረሰው ጥቃት አርብ ዕለት በመስጂድ ውስጥ በጁምዓ ጸሎት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ጥቃቱ መፈጸሙን የዓይን እማኞቹ ተናገረዋል።

ይህንን የአካባቢው ነዋሪዎችን ሪፖርት ከአካባቢው ባለስልጣናት ለማረጋገጥ ሮይተርስ በስልክ ጥሪ እና በጽሁፍ መልዕክቶች ጥረት ቢያደርግም ምላሽ አለማግኘቱን አስታውቋል።

የሩዋን ጁማ አካባቢ ነዋሪዎች ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ ለታጣቂ ሽፍቶቹ ዘጠኝ ሚሊየን የናጄሪያ ኒያራ ወይም 21,000 የዩናይትድ ስቴትስ ዶላር፣ ትምባሆ እና ነዳጅ ከፍለው እንደነበር አስታውቀዋል።