በአፋር ተይዘው ያሉ የትግራይ ተወላጆች ለሞት  እና  ለበሽታ ተጋልጠናል አሉ

New front in Ethiopian war displaces thousands, hits hopes of peace talks

ከአፋር ክልል አብዓላ ከተማ ታፍሰን ሰመራ የሚገኝ ማጎሪያ ውስጥ እንገኛለን ያሉ የትግራይ ተወላጆች ያለጠያቂና ተመልካች ከአምስት ወራት በላይ መያዛቸውን ለቪኦኤ ተናገሩ። የትግራይ ተወላጆቹ “ለሞት እና ለበሽታ ተጋልጠናል” ብለዋል።

ባለፈው ታኅሳስ አብዓላ ከተማ አካባቢ በትግራይ ታጣቂዎችና በፌደራል መንግሥቱ በሚደገፉ ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ መታፈሳቸውንና መወሰዳቸውን የሚናገሩት እነዚሁ በሺህዎች እንደሚቆጠሩ የሚናገሩት ሰዎች ምግብና ውኃ፣ ህክምና ባለማግኘት እና መጠለያ በማጣት እየተንገላቱ መሆናቸውን ገልፀዋል።

እስካሁንም 76 ሰዎች ከመካከላቸው መሞታቸውን ተናግረዋል።

ከአፋርና ከፌደራል ባለሥልጣናት እንዲሁም ከሌሎች ስለጉዳዩ ዕውቀት አላቸው ከተባሉ አካላት ምላሽና ማብራሪያ ለማግኘት በተከታታይ ቀናት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ ገልፆ የትግርኛ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረባ ገብረ ገብረመድህን ያጠናቀረውን ዘገባ አሉላ ከበደ ያቀርበዋል።

ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ