አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ቃለ መሃላ ፈጽመው በትረ ሥልጣኑን ተረክበዋል
Your browser doesn’t support HTML5
“ፈርማጆ” በሚለው ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት አዲሱ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ቃለ መሃላ ፈጽመው በትረ ስልጣኑን ተረክበዋል። በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ሀገሪቱን ለማረጋጋት፣ ሰላም ለማስፈንና በአሁኑ ወቅት በርካታ ዜጎችን ለተረጂነት ያጋለጠው ድርቅ ያስከተለውን ረሃብ ለመቋቋም ሕዝቡ፣ መንግስቱና አጋሮቻቸው አብረው እንዲሠሩ ጠይቀዋል።