የኦርላንዶ የጅምላ ግድያ ሰለባ ቤተሰቦች ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር ተነጋገሩ

  • ሰሎሞን ክፍሌ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በትላንትናው ዕለት ፍሎሪዳ ክፍለ-ግዛት ኦርላንዶ ከተማን ጎብኝተዋል፥ ባለፈው እሁድ በአንድ ተመሳሳይ ጾታ ባላቸው ሰዎች በሚዘወተር የምሽት ክበብ ውስጥ የጅምላ ግድያ ሰለባ የሆኑትን ቤተሰቦች በግል አነጋግረዋል። በዚያ ጥቃት 49 ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች 53 መቁሰላቸው ይታወቃል።

ፕሬዝዳንት ኦባማ በዚሁ ጉብኝታቸው ወቅት፥ የሰለባዎቹን ቤተሰቦችና በሕይወት የተረፉትን ያጽናኑ ሲሆን፥ የጦር መሣሪያ በወንጀለኞች እጅ እንዳይገባ መከላከል የሚያስችል እርምጃ እንዲወሰድ ከዚህ ቀደም ያቀረቡትን ተማጽኖም በድጋሚ አስተጋብተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኦርላንዶ የጅምላ ግድያ ሰለባ ቤተሰቦች ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር ተነጋገሩ