በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

ቅዳሜ 27 ጁላይ 2024

አርሶ አደሩ ጀምስ ሹማ በዚምባብዌ በድርቅ ሳቢያ በደረቀው የሰብል ማሳው መካከል ቆሟል፤ ደቡብ ምዕራብ ዚምባብዌ የማንግዌ ወረዳ አርብ፣ መጋቢት 22፣ 2024።
አርሶ አደሩ ጀምስ ሹማ በዚምባብዌ በድርቅ ሳቢያ በደረቀው የሰብል ማሳው መካከል ቆሟል፤ ደቡብ ምዕራብ ዚምባብዌ የማንግዌ ወረዳ አርብ፣ መጋቢት 22፣ 2024።

የአየር ንብረት ለውጥ እና የዓለም ሕዝብ ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት መጨመር የምግብ ዋስትናን አደጋ ላይ ሊጥል የመቻሉ ዕጣ እያነጋገረ ነው። እንደ ባለሞያዎችም እምነት የዓለም ህዝብ ቁጥር ከ10 ቢሊዮን በላይ ሲደርስ የሰብል ምርት በአንጻሩ በ30 በመቶ ሊቀንስ ይችላል።

መሀመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ የመንግሥታቱን ድርጅት የዓለም ሕዝብ ቀን አስታኮ ባጠናቀረው ዘገባ እንደጠቆመው፤ ሁኔታው በተለይ በአፍሪካ የሚኖረውን ተጽዕኖ ለመቀነስ፤ በግብርናው ዘርፍ የሚደረግ ለውጥ ብቸኛው አማራጭ ነው።

ለዝርዝሩ አሉላ ከበደ።

ፎት ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም
ፎት ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም

በሱዳን የተከሰተው ረሃብ ከቸነፈር ደረጃ ላይ መድረስ ያለመድረሱን ለመወሰን የመንግሥታቱ ድርጅቶች የተለያዩ ተቋማት እና ሌሎች የእርዳታ ድርጅቶች ባቀረቡት የቅድመ ትንበያ ውጤት መሰረት፣ ከ756 ሺሕ ሕዝብ በላይ ለከፋ የምግብ እጥረት ሊጋለጥ እንደሚችል ተሰግቷል።

የመጀመሪያው የትንበያ አሃዞች፤ እስካለፈው ግንቦት 24, 2016 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ በጦርነት በተበታተነችው አገር ውስጥ የታየውን 'በፍጥነት እያሽቆለቆለ ያለ ሁኔታ የሚያመላክቱ ናቸው’ ተብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከትላንት በስቲያ ረቡዕ በሰጡት አስተያት፣ በዓለም ግዙፍ የሰብአዊ ቀውስ በተከሰተበት የሱዳን ምስቅልቅል 12 ሚሊዮን ሕዝብ ከቀዬው መፈናቀሉን ተናግረዋል።

"በአንዳንድ ግዛቶች እጅግ መጠነ ሠፊ የረሃብ አደጋ በተንሰራፋበት ባሁኑ ወቅት ነዋሪዎች አስፈላጊ አገልግሎቶችን እና መድሃኒቶችን የማያገኙ በመሆናቸው ለሕልፈት እየተዳረጉ ነው" ሲሉ አክለዋል።

በተቀናጀ የምግብ ዋስትና የደረጃ ምደባ አሰራር መሰረት በሰኔ እና በመስከረም ወር መሃከል ባለው ጊዜ ውስጥ ቁጥራቸው 756, 000 የሚጠጉ ሰዎች የከፋ ውድመት ሊያስከትል በሚችለው ደረጃ 5 ውስጥ እንደሚገቡ የቅርብ ጊዜያቱ ትንበያዎች ጠቁመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሱዳኑ ብሔራዊ ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ባለፈው ዓመት የሚያዝያ ወር የተቀሰቀሰው ውጊያ አሁንም ተባብሶ መቀጠሉ ታውቋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG