በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጄኮብ ዙማ መንግሥታዊ የሙስና ወንጀልን በተመለከተ ምስክርነታቸውን ላለመቀጠል ወሰኑ


የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጄኮብ ዙማ
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጄኮብ ዙማ

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጄኮብ ዙማ፣ መንግሥታዊ የሙስና ወንጀልን በተመለከተ የጀመሩትን ምስክርነት ላለመቀጠል መወሰናቸው ተነገረ።

የዙማ ጠበቆች በዛሬው ቀን በሰጡት ቃል፣ ደንበኛቸው ምስክርነታቸውን በሚሰጡበት ወቅት በአግባቡ አልተስተናገዱም ብለዋል።

ጠበቃ ሙዚ ሲክሃክሃኔ ሲናገሩ፣ ዙማ ከመጀመሪያውም የተስተናገዱት ልክ እንደ ተከሳሽ ነበር ብለዋል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዙማ በበኩላቸው፣ ምንም ዓይነት ሙስና እንዳልፈፀሙ አስተባብለው፣ ነገሩ የተወጠነውም የርሳቸውን ታዋቂነት ለማጠልሸት ብሎም ሕይወታችን ለማጥፋት እንደሆነ ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG