አዲስ አበባ —
እሥር ቤት ውስጥ የሚገኙት ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ፀሐፍት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ ከዚህ በኋላ ጉዳያቸውን እንዳይመለከቱ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል፡፡
አቤቱታ ያቀረቡባቸው ዳኛ ግን በራሣቸው ፈቃድ ጉዳዩን ላለማየት መወሰናቸውን ገልፀዋል።
ከተከሳሾቹ አንዱ አቤል ዋበላ እሥር ቤት ውስጥ ግፍ እንደተፈፀመበት ለፍርድ ቤቱ አቤት ብሎ መፍትሔ እንዲሰጠው አመልክቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አመሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡