በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‘የዞን-9 ጦማሪያንን ፍቱ!’ ዓለምአቀፍ የትዊተር ዘመቻ


‘የዞን-9 ጦማሪያንን ፍቱ!’ ዓለምአቀፍ የትዊተር ዘመቻ
‘የዞን-9 ጦማሪያንን ፍቱ!’ ዓለምአቀፍ የትዊተር ዘመቻ

ኢትዮጵያ ውስ እስር የሚገኙ የኢንተርኔት አምደኞችና ጋዜጠኞች “ይፈቱ!” የሚል የትዊተር ዘመቻ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው፤ በትዊተር ቋንቋ ‘trend (ትሬንድ) አድርጓል’።




ግሎባል ቮይስስ
ግሎባል ቮይስስ

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኢትዮጵያ ውስ እስር የሚገኙ የኢንተርኔት አምደኞችና ጋዜጠኞች “ይፈቱ!” የሚል የትዊተር ዘመቻ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው፤ በትዊተር ቋንቋ ‘trend (ትሬንድ) አድርጓል’።

ለሃያ ቀናት ያህል ክሥ ሳይመሠረትባቸው በማዕከላዊ እሥር ቤት የሚገኙት “ወጣት ፀሃፊዎችና ጋዜጠኞች ይፈቱ! የኢትዮጵያ መንግሥት የመናገር ነፃነትን ያክብር! ጋዜጠኝነት አሸባሪነት አይደለም! መጦመር ወንጀል አይደለም!” የሚሉ መልዕክቶች በማኅበረሰብ መገናኛው ትዊተር ዛሬ በዓለም ዙሪያ የተስተጋቡ መልእክቶች ናቸው።

ከናይጀሪያ፣ ታንዛንያና ዩናይትድ ስቴትስ የተውጣጡ ግሎባል ቮይስስ የሚባል የፀሃፊዎች ኅብረት አባላት ናቸው ለአራት ሰዓት የዘለቀውን የኢንተርኔት ዘመቻ ያካሄዱት። ውጤቱ ስኬታማ መሆኑን አዘጋጆቹ ለቪኦኤ ገልጸዋል።

በተለያዩ የዓለም ጫፎች ዛሬ በ140 ፊደላት የተቀመሩ አጫጭር ጽሁፎች ሲሠራጩ፤ Tweet ReTweet Favor ሲደረጉ ውለዋል። ተምብለርን ጨምሮ በትዊተር ሰዎች መፈክር ይዘው ፎቶ እየተነሱ፤ በዘመቻው ተሣትፈዋል።

ታዋቂው የአሜሪካ የመናገር ነጻነት ተቋም ፔን አሜሪካ በትዊተር ዛሬ የለቀቀው ፎቶም የዞን-9ን የኢንተርኔት ጦማርያን ልቀቁ የሚል መልዕክት አስተጋብቷል። ይህ ድርጅት ወኅኒ ለሚገኘው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የዓመቱ ክብር የሚገባው ሰው በማለት ሽልማት ሰጥቶታል።

የጋዜጠኞች ደኅንነት ተከራካሪው ድርጅት /Committee to Protect Journalists – CPJ/ ባጠናቀረው መረጃ መሠርት በኢትዮጵያ 18 ጋዜጠኞች እሥር ላይ ይገኛሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG