በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ያለ ለፍርድ የታሰሩት የዚምባቡዌ ተቃዋሚ መሪ በነጻ ተሰናበቱ


ጃብ ሲካላን
ጃብ ሲካላን

የዚምባብዌ ፍርድ ቤት ታዋቂዎን ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ጃብ ሲካላን ትናንት ማክሰኞ በነጻ አሰናብቷል፡፡ ሲካላ የተፈቱት የፍርድ ሂደት ከመጀመሩ አስቀድሞ ያለ ፍርድ 600 ቀናት ከታሰሩ በኋላ ነው፡፡

የተቃዋሚው መሪ የታሰሩት እኤአ በ2022 ሲሆን የታሰሩበትም ምክንያት ገዥው ፓርቲ አንድ የተቃዋሚዎች መብት ተሟጋችን ገድሏል በሚል ህዝባዊ ብጥብጥ በማስነሳት በቀረበባቸው ክስ ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ በእስር ላይ ያሳለፉትን ረጅም ጊዜ ግምት ውስጥ በማስገባት ከእስር እንዲፈቱ የሁለት አመት (የታሰሩበትን ያህል) የእስር ቅጣት ወስኖባቸዋል።

ምንም እንኳ አሁን በነጻ የተለቀቁ ቢሆንም ጠበቃቸው ስለውሳኔው ይግባኝ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል፡፡

የዜጎች ጥምረት ለለውጥ ፓርቲ መሪ የሆኑት ታዋቂው የፖለቲካ ተቃዋሚ ሲክሃላም እ.ኤ.አ. በ1999 ፖለቲካ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ በርካታ የእስር ታሪክ አላቸው፡፡

የቅጣት ውሳኔውን ከመቀበል ይልቅ ሙሉ ለሙሉ ነጻ መሆንን በመምረጥ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የመጠየቅ እቅድ እንዳላቸው ሲክሃላም አክለው ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG