መቀሌ —
ዛሃፍታ ተክኤ የ24 ዓመት ወጣት ናት፡፡
ዛሃፍታ በትግራይ ክልል ከኣኵስም ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው የገጠር መንደር ውስጥ ነው ተወልዳ ያደገችው፡፡
ገና ጨቅላ ሕፃን ሆና ከወላጆቿ የቀረበላትን የጋብቻ ጉትጎታ በብርቱ እየተቃወመች ስምንተኛ ክፍል ደረሰች፡፡
ዛሃፍታ በትግራይ ክልል ስምንተኛ ማጠናቀቂያ ክፍል ላይ የሚሰጠውን ብሔራዊ ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት ካስመዘገቡት ተማሪዎች አንዷ በመሆን ታጭታ በቃልአሚኖ ልዩ ትምህርት ቤት ገብታ ትምህርቷን ቀጠለች፡፡
በ10ኛ ክፍል መልቀቅያ ብሔራዊ ፈተና ደግሞ አራት ነጥብ አግኝታ ከክልሉ ተፈታኞች አንደኛ፤ ከኢትዮጵያ ደግሞ ከሴት ተፈታኞች አንደኛ በመውጣት በድጋሚ ጉብዝናዋን አሣየች፡፡
ዛሃፍታ 11ኛ ክፍል እያለች አሜሪካ ሄደው የባህልና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ልውውጥ ላይ እንዲሣተፉ ከመላ ኢትዮጵያ ከተመረጡት ዘጠኝ ወጣቶች አንዷ ሆና አሜሪካ ውስጥ ለአንድ ዓመት ቆይታለች፡፡
በቆይታዋ ጊዜ ታድያ ከተለያዩ ሰዎች የተደረገላትን ማበረታቻ በመጠቀም ገንዘብ በማሰባሰብ ተወልዳ ባደገችበት የገጠር መንደር ውስጥ ሁለት ጉድጓዶች እንዲቆፈሩ በማድረግ ኅብረተሰቡ ንፀህ የመጠጥ ውኃ እንዲያገኝ አስችላለች፡፡
ግርማይ ገብሩ ከዛሬይቱ አጥቢያ ኮከብ ዛሃፍታ ተክኤ ጋር ያደረገው ውይይትን በተያያዘው የድምፅ ፋይል ላይ ያገኙታል፤ ያዳምጡት፡፡