በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወጣት አፍሪካዊያኑ መሪዎች የዋሽንግተን ጉባዔ - ሁለተኛ ቀን


please wait

No media source currently available

0:00 0:17:54 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ እንዲሁም የኮንግረስ አባላት ጋር አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ስላላት ግንኙነት፣ የወጣቶች ሚና፣ አልፎም በአፍሪካ የወደፊት ዕድገትና ፈተናዎች ዙሪያ ትናንት ሲወያዩ የዋሉት 500 የአፍሪካ ወጣቶች ዛሬ ደግሞ ለውጥ እንዴት ሊያመጡ እንደሚችሉ ሲነጋገሩ ውለዋል፡፡

ወጣቶቹ የለውጥ መሪዎች እንደሆኑ፤ ለዚህም የተጠናከረ ድጋፍ እንዳላቸው ፕሬዝደንት ኦባማ ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለት ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ስልታዊ ውይይቶችን እርስ-በርስ ሲያካሂዱ ነው የዋሉት።

በሌላ በኩል ደግሞ ከኢትዮጵያዊያኑ ተሣታፊዎች አንዱና በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የተጀመረውና በዚህ ዓመት በታላቁ ደቡብ አፍሪካዊ መሪ ኔልሰን ማንዴላ ስም የተሰየመው የማንዴላ ዋሺንግተን የትምህርትና የልምድ ዕድል ተሣታፊ የሆነው ሚካኤል አዲሱ ከ500ዎቹ ወጣቶች መካከል ተመርጦ የሚሰጥ የስራ ማጠናከሪያ ገንዘብ ተሸላሚ ሆኗል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የሄኖክ ሰማእግዜርን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG