በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሁቲ አማጽያን የያዟቸውን ወደቦች ለመልቀቅ የተደረሰው ስምምነት መጣሱ ተገለፀ


የሁቲ አማጽያን የያዟቸውን ሁለት ወደቦች ለመልቀቅ የደረስነውን ስምምነት ጥሰዋል ሲሉ የመን ሸሪኮቿ ሳዑዲ አረቢያና የተባበረው አረብ ራቢጣ ከሰዋል።

ሽምቅ ተዋጊዎቹ የገቡትን ቃል እንዲጠብቁ ይጠይቁ ዘንድም የሦስቱ ሀገሮች አምባሳደሮች ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒኦ ጉቴሬዥ ደብዳቤ ልከዋል።

“የሁቲ አማጽያን ከሣሊፍና ራሥ ኢሣ ወደቦች አንወጣም ሲሉ ድንገትና ምክንያቱ ያልተገልፀ እምቢተኝነታቸውን ባለፈው ሣምንት የገለጹት ለወራት ያህል ጉዳዩን የማጓተት ዘዴ ሲጠቀሙ ከቆዩ በኋላ በመሆኑ ያልተጠበቀ አይደለም” ይላል የአምባሳደሮቹ ደብዳቤ።

አማጽያኑ በወደቦቹ ዙሪያ ምሽጎችን በመቆፈርና ወታደራዊ ይዞታዎችን በማጠናከር ላይ ናቸው ሲሉ በኢራን የሚታገዙትን የሁቲ ሽምቅ ተዋጊዎች ከየመን ለማስወጣት የሚጥሩት ሦስቱ ሃገሮች ይከሳሉ።

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ከሽምቅ ተዋጊዎቹ ወገን እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

ሁሉም ወገኖች የደረሱትን ስምምነት ተግባራዊ ያደርጉ ዘንድ - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ አስገንዝበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG