በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓመቱ የዲሞክራሲ ፊልም ውድድር አሸናፊ ያሬድ ሹመቴ


“እፍረት አልባ ጨዋታ” ያሬድን ለሽልማት ያበቃው የ3 ደቂቃ ፊልም ነው

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የዲፕሎማሲ ክፍል ጋባዥነት በዓለም ዙሪያ በያመቱ በዲሞክራሲ ላይ ባጠነጠኑ ርዕሶች ላይ ያተኮረ የቪዲዮ ፊልም ውድድር ይካሄዳል፡፡

በዘንድሮው ዓለም አቀፍ ውድድር ለአሸናፊነት ከበቁ አምስት ሠዎች አንዱ ለመሆን የበቃው ኢትዮጵያዊው ፊልም ሠሪ ያሬድ ሹመቴ ሽልማቱን ለመቀበል ባለፈው ጳጉሜ መጨረሻ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ተገኝቶ ነበር፡፡

በዚህ ውድድር ከያሬድ ሌላ አሸናፊ የሆኑት ከካምቦዲያ፥ ኢንዶኔዥያ፥ ኢራንና ኔፓል የተወዳደሩ አራት ፊልም ሰሪዎች ናቸው።

ያሬድ ስለ ፊልም ሀሳቡ እና ስራው ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የመፅሄት ፕሮግራም ጋር ያደረገውን ቆይታ አሜሪካ ድምጽ ራድዮ የገለፀውን ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG