በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም የንግድ ልውውጥ ድርጅት የሚኒስትሮች ጉባዔ በኬንያ


ኬንያ ዳብሊው ቲ ኦ (WTO) በመባል የሚታወቀው የዓለም የንግድ ልውውጥ ድርጅት ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ የሆነው አካል የሚኒስትሮች ጉባኤን እያስተናገደች ነው። የዶሃ የንግድ ድርድር ዙር በአፍሪቃ ምድር ሲካሄድ ለመጀመርያ ጊዜ ሲሆን በታዳጊ ሀገሮችና በበለጸጉት የዓለም ሃገሮች መካከል ያለው የንግድ ሚዛን መዛባትን በሚመለከት አዎንታዊ ውጤት ሊያመጣ ይችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ልኡካኑ ጠቁመዋል።

የዓለም የንግ ድርጅት የዶሀ የልማት አጀንዳን የጀመረው እአአ በ 2001 አም ሲሆን (ከ 14 አመታት በፊት ማለት ነው) የድርድሩ ሂደት ለ 14 አመታት ያህል ተራዝሟል። የዶሀው አጀንዳ ታዳጊ ሀግሮች በአለም ኢኮኖሚ ውስጥ በበለጠ እንዲዋሀዱ ለማስቻል የንግድ ገደቦች እንዲነሱ ይፈልጋል።

ዲዮዳት ማሓራጅ ህንድንና በርካታ ከሰሀራ በመለስ ያሉትን ትልልቅ ኢኮኖሚ ያላቸውን የአፍሪቃ ሀገሮች የሚያቅፈውን የ 53 ሀገሮች የጋራ ገበያ ምክትል ዋና ጸሃፊ ናቸው። አፍሪቃ ውስጥ ያለውን የንግድ ሚዛን መዛባትን ለማስተካከል ከተፈለገ በመጀመርያ ደረጃ ሀገሮች የውስጥ ፖሊሲያቸውን መለወጥ አለባቸው ይላሉ።

“ከመላ ገበያህ የምታቀርበው ነገር ከሌለ ተገቢ ንግድ ለማካሄድ አይቻልም። የአፍሪቃን አጠቃላይ ንግድ ለማቅረብም ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ የሚደረገው የንግድ ልውውጥ ካለ ምንም ችግር እንዲከናወን የንግድ መተላለፍያ ኮሪዶር መክፈት ይኖርብናል።”

የዚህ አመቱ ጉባኤ ናይሮቢ ከመጀመሩ በፊት ዋና አከራካሪ ነጥብ ሆኖ የነበረው ለ 14 አመታት ያህል በተራዘመው ድርድር እንቀጥል ወይስ በአዲስ መልክ እንጀምር የሚል ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ (United States) እና አውሮፓ በአዲስ መልክ እንዲጀመር ይፈልጋሉ። ኬንያንና ደቡብ አፍሪቃን የመሳሰሉት ሃገሮች ደግሞ የዶሀው ድርድር እልባት እንዲያገኝ ይፈልጋሉ።

ኮሜሳ (COMESA) ማለት የምስራቅና የደቡባዊ አፍሪቃ የጋራ ገበያ ምክትል ዋና ጸሃፊ ኪፕየጎ ቸሉገት (Kipyego Cheluget) ብዙ መፈታት ያለባቸው ነገሮች አሉ ይላሉ።

“ይህ ቀጣይ ሂደት ነው። በጣም ከባድና ውስብስብ ጉዳይ ነው። ስለሆነም ከናይሮቢው ጉባኤ በኋላም ችግሩ ሁሉ ይፈታል ብለን በሙሉ መተማመን ልንናገር እንችላለን በሚለው ነጥብ ላይ እርግጠኛ አይደለሁም። አንዳንዶቹን ተግዳሮቶች የመፍታት ሂዳት የሚጀመርበት ሊሆን ይችላል።”

የበለጸጉት ሀገሮች የእርሻ ድጎማዎች መስጠቱን እንዲያቆሙ የሚጠይቀው በማደግ ላይ ካሉት ሀገሮች የሚቀርበው ግፊት በወቅቱ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ አብይ ቦታ ይይዛል ተብሎ ይገመታል።

አንዳንዶቹ የአልም የንግድ ድርጅት ለሀብታም ሀገሮቹ ያዳላል ያሚል ቅሬታ ያሰማሉ። የደቡባዊና የምስራቅ የንግድ ኢንፎርሜሽንና ድርድር ተቋም ዋና ስራ አስፈጻሚ ያሽ ታንደን የሚኒስትሮቹ አካል ለአፍሪቃ መፍትሄ አያመጠም ይላሉ።

“የአለም የንግድ ድርጅት ዳብልው ቲ ኦ (WTO) እኩልነትን አያንጸባርቃም። ስልጣኑ ከድርጅቱ ሴክሬታሪያት ጋር በተሳሰሩ የምዕራብ ሀገሮች እጅ ላይ ነው ያለው። ሴክረታርያቱ ደግሞ

በአፍሪቃ ላይ ያለው አመላካከት ወግንተኛ ነው። ስለሆነም አሁን ነጻ ንግድ በሚለው ነገር ላይ የመግፋታቸው ጉዳይ ባኛ ላይ ሚዛን ያልጠበቀ ነገር ነው።”

ኬንያ ውስጥ የሚካሄደው የአራት ቀናት ጉባኤ በመጪው አርብ ያበቃል። ከአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ለኒ ሩቫጋ (Lenny Ruvaga) ከናይሮቢ የተላከውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለ። ዘገባውን ለመኣዳመጥ የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የዓለም የንግድ ልውውጥ ድርጅት የሚኒስትሮች ጉባዔ በኬንያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:35 0:00

የዓለም የንግድ ልውውጥ ድርጅት የሚኒስትሮች ጉባዔ በኬንያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:50 0:00

XS
SM
MD
LG