በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መስኮት ይክፈቱ፤ ቲቢን ያቁሙ


"መስኮት ይክፈቱ፤ ቲቢን ያቁሙ" - የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ፶ኛ ዓመት ፀረ-ቲቢ የእግር ጉዞ ፖስተር
"መስኮት ይክፈቱ፤ ቲቢን ያቁሙ" - የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ፶ኛ ዓመት ፀረ-ቲቢ የእግር ጉዞ ፖስተር

መጋቢት 15 የዓለም የትዩበርኩለስስ ወይም ቲቢ ቀን ሆኖ አልፏል፡፡




please wait

No media source currently available

0:00 0:10:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ቲቢ በዓለማችን ላይ የሰው ልጅ ጠላት ሆነው ከተንሠራፉ ደዌዎች አንዱ ሲሆን በየዓመቱ ወደአንድ ሚሊየን ተኩል ሰው ይጨርሣል፡፡ በየዓመቱ ደግሞ 9 ሚሊየን ሰው ቲቢ አምጭውን ሕዋስ ከአየር እና በንክኪም እያገኘ ቲቢ በሰውነቱ ውስጥ ያለውን ሰው ይቀላቀላል፡፡

ቲቢ ከሚያስከትለው ጉዳት ታዲያ እጅግ የበዛው የሚደርሰው በድኃ ሃገሮች ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ አቆጣጠር መጋቢት 15/1976 ዓ.ም ጀርመናዊው ሣይንቲስት ዶ/ር ሮበርት ኮች ማኮባክቴርየም ትዩበርኩለሲስ የሚባለውን ተውሣክ አገኙና “ሣንባ ነቀርሣ” እየተባለ ሲጠራ የቆየውን ትኩሣት፣ ደም የቀላቀለ ሣልና የበረታ ድካም የሚያስከትለውን በሽታ የሚያመጣው ምን እንደሆነ ታወቀ፡፡

ከዚያ ቀን ጋር ተያይዞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባሣለፈው ውሣኔ መሠረት ትዩበርኩለሲስ የሚያስከትለውን ችግር አጉልቶ ለማሣየት እና በዓለም ዙሪያም ቲቢን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለማሣደግ ታስቦ ዕለቱ የቲቢ ቀን ሆኖ እየታሰበ ይውላል፡፡
ቲቢን ያቁሙ
ቲቢን ያቁሙ

ስለቲቢ ስንነጋገር ሰዉ ማወቅ ያለበት አምስት አበይት ጉዳዮች ብሎ የዓለም የጤና ድርጅት የዘረዘራቸው አሣሣቢ አካባቢዎች አሉ፡፡
እነዚህም፡-
1. ቲቢ ባክቴርያ አመጣሽ ሆኖ በአየር በቀላሉ ይተላለፋል፤
2. ትዩበርኩለሲስ በዓለም ዙሪያ ለሕክምና አዳጋች እየሆነ ነው፤
3. ትዩበርኩለሲስ ዓለምአቀፍ አደጋ ነው፤
4. የሰውነታቸው የተፈጥሮ መከላከያ ደካማ የሆነ ሰዎች ለቲቢ ይበልጥ የተጋለጡ ናቸው፤
5. ለህክምና የማይበገረው ቲቢ ሌሎች የጤና አገልግሎቶችንና ተቋማትንም ወደኋላ ይጎትታል፤ የሚሉ ናቸው፡፡

በዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት መሠረት እአአ በ2011 ዓ.ም ብቻ ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ባልተያያዘ ሁኔታ ከ11 ሺህ እስከ ሃያ ሺህ የሚሆን ሰው በቲቢ ብቻ ሞቷል፡፡ በዚያው ዓመት ደግሞ ከ16ዐ እስከ 280 ሺህ የሚሆን ሰው ለቲቢ እንደአዲስ ተጋልጧል፤ ወይም ተይዟል፡፡
ነዋይ ፀጋዬ፤ የአዲስ አበባ የጤና ጋዜጠኞች ኢኒሼቲቭ ሊቀመንበር
ነዋይ ፀጋዬ፤ የአዲስ አበባ የጤና ጋዜጠኞች ኢኒሼቲቭ ሊቀመንበር

ይህንኑ የዓለም ቲቢ ቀንን ምክንያት በማድረግ ከዕለቱ በፊትና በዕለቱም በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ቀደም ሲል ጀምሮ ከተለያዩ ሥልጠናዎች፣ አውደጥናቶችና ሌሎችም መድረኮች ሰፊ ግንዛቤ ያዳበሩ ጋዜጠኞች ዘገባዎችን ለሕዝብ ሲያቀርቡ እንደነበር፣ ወደፊትም እንደሚቀጥሉ የአዲስ አበባ የጤና ጋዜጠኞች ኢኒሼቲቭ ሊቀመንበር ነዋይ ፀጋዬ ለቪኦኤ ገልጿል፡፡

ተጨማሪ እና ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG