በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ስደተኞች ቁጥር ከሃምሣ ሚሊየን በለጠ


በዓለም ዙሪያ ባለፈው የአውሮፓ ዓመት መጨረሻ ላይ ከሃምሣ ሚሊየን የሚበልጥ ሰው በግጭቶች ምክንያት በኃይል መፈናቀሉን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር አስታውቋል፡፡



ስደት
ስደት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:16 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በዓለም ዙሪያ ባለፈው የአውሮፓ ዓመት መጨረሻ ላይ ከሃምሣ ሚሊየን የሚበልጥ ሰው በግጭቶች ምክንያት በኃይል መፈናቀሉን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር አስታውቋል፡፡

ዛሬ - ሰኔ 13 የዋለውን የዓለም ስደተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ዩኤንችሲአር ባወጣው ሪፖርቱ ይህ ቁጥር የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዘመን ስደትን ለመጀመሪያ ጊዜ በልጦ መገኘቱንም አመልክቷል፡፡

ከዓለም ስደተኞች 86 ከመቶ የሚሆኑት የሚኖሩት በማደግ ላይ ባሉ ሃገሮች ውስጥ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገልፀው ይህ ምዕት ዓመት ከባተ አንስቶ ይህ እጅግ ከፍተኛ የሆነ መጠን መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በታዳጊ ሃገሮች ውስጥ የተጠለለው ስደተኛ ብዛት ሚዛን የዛሬ አሥር ዓመር ሰባ ከመቶ እንደነበር ጉቴሬስ ተናግረዋል፡፡
ስደት
ስደት
“ስለዚህም የምናየው የስደት አካሄድ ስደተኛው እየበዛ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ከሚሰደደውም በታዳጊዎቹ ሃገሮች ውስጥ ህይወቱን የሚቀጥለው ቁጥርም እንደዚያው እየበዛ መሆኑን ነው፡፡” ብለዋል የዓለሙ የስደተኞች ተቋም ኃላፊ፡፡

ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ቁጥር ያለው ስደተኛ የሚወጣባቸው ሶማሊያና ሶሪያ ከዓለም 16 ሚሊየን ድንበር አቋራጭ ስደተኛ የሁለቱ ሃገሮች ድምር ከግማሽ እንደሚበልጥ፤ በአፍሪካም ከአንድ ሚሊየን በላይ ስደተኛ የወጣባቸው ሱዳንና ኮንጎ ከአሥሩ የስደት ምንጭ ሃገሮች መካከል እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡ ከኤርትራ 308 ሺህ ስደተኞች የወጡ ሲሆን በዚህም በዓለም አሥረኛ የስደት ምንጭ ሃገር ሆናለች፡፡
ስደት
ስደት

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ በማስተናገድ 1.6 ሚሊየን ሰው ያስጠለለችው ፓኪስታን አንደኛ ስትሆን በአፍሪካ ኬንያ፣ ቻድና ኢትዮጵያ ቀዳሚዎቹ ስደተኛ ተቀባይ ሃገሮች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ እኩሌታቸው ከሶማሊያ የሆነ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ከሁሉም ጎረቤቷቿ የገቡ ስደተኞችን ማስጠለሏን የዩኤንኤችሲአር የኢትዮጵያ ቢሮ አስታውቋል፡፡
ስደት
ስደት

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ ከሚባሉት ስደተኛ አስጠጊ ሃገሮች አንዷ ብትሆንም እራሷም በሌላ በኩል የስደት ምንጭ ከሚባሉ ሃገሮች ውስጥ የተሰለፈች መሆኗ ይታወቃል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG