በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም መሪዎች ጉባዔ በኒውዮርክ


የዓለም መሪዎች ስለአየር ንብረት ለውጥ ለመወያየት ዛሬ በኒውዮርክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባዔ ይዘዋል።

ሳይንቲስቶች የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትልን መዘዝ ለመቋቋቁም የሚያስፈሉልጉትን ዕርምጃዎች ለማከናወን ጠንከር ብሎ መንቀሳቀስ የግድ መሆኑን ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።

ሙሉ ቀን በሚካሄደው ጉባዔ ወደስልሳ የሚሆኑ ፕሬዘዳንቶች እና ጠቅላይ ሚኒስትሮች ንግግር ያደርጋሉ።

ከሚነሱት ነጥቦች መካከል ከሰል መጠቀም እየቀረ ታዳሽ የኃይል ምንጮችን መጠቀም የተፈጥሮ አደጋዎችን መከላከል እና ሲደርሱም ምላሽ መስጠት እንዲሁም ለአየር ንብረት ለውጥ ዕርምጃዎች አስፈላጊ ገንዘብ ምደባ የመሳሰሉት ይገኙበታል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በጉባዔው ላይ ከሚሳተፉት መካከል ያልነበሩ ቢሆንም በድንገት ብቅ ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በውህዳን የሃይማኖት ተከታዮች በተለይ በክርስቲያኖች ላይ የሚደርስ ጭቆናን በሚመለከት ስብሰባ ላይ ይካፈላሉ። ከዚያም ከፓኪስታን ከግብፅ፣ ከደቡብ ኮሪያ፣ ከፖላንድ፣ ከኒውዚላንድ እና ከሲንጋፖር መሪዎች ጋር ለየብቻ ይወያያሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ ኣንቶንዮ ጉቴሬዥ ስለአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔው ትልቅ ቦታ አጉልተው ሲናገሩ ቆይተዋል። ከመሪዎች የሚጠበቀው ቆንጆ ንግግር ሳይሆን ተጨባጭ ዕቅድ ነው ሲሉ አሳስበዋል።

የዛሬው ጉባዔ ከመከፈቱ አስቀድሞ የመንግሥታቱ ድርጅት በዓለም የሜቴሮሎጂ ድርጅት የተጠናቀረ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። የአየር የካርቦን ብከላ፣ የባህር ጠለል ከፍታ፣ የዓለም አየር ሙቀት እየተባባሰ መሆኑ እና የበረዶ ንጣፎችም እየሳሱ መሆኑ በሪፖርቱ ተመልክቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG