በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ጋር የበካይ ጋዝ ልቀት ቅነሳ ሥምምነት ተፈራረመች


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ

በሥምምነቱ የዓለም ባንክ የደን እንክብካቤና ጥበቃን ጨምሮ ዘላቂ የደን መሬት አያያዝን አጠቃቀሞችን በመተግበር የካርበን ልቀትን ለመቀነስ የሚያግዝ 40 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የዓለም ባንክ የባዮካርበን ፈንድ መርሃ ግብር የደን መመናመንን በመቆጣጠር እና ውጤታማ የደን ልማትና ክብካቤ በማድረግ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ በማኅበረሰብ ደረጃ የሚደረጉ ጥረቶችን ዕውቅና ሰጥቶ በመደገፍ ዕገዛ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።

የካርቦን ልቀት ቅነሳ ግዢው ሥምምነት ማኅበረሰቦች መንግሥት እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የካርቦን ልቀትን እንዲቀንሱ በደን እንክብካቤ እና በሊሎችም የተፈጥሮ አካባቢን የማይጎዱ አሰራሮች አማካይነት ልቀቱን እንዲቆጣጠሩ ለማስቻል የሚውል እስከ አርባ ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ የሚመድብ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ይህ የካርቦን ልቀት ቅነሳ ግዢ ድጋፍ ከዘላቂ የደን እንክብካቤ በተያያዘ ሲመደብ በዐይነቱ የመጀመሪያ ሲሆን በኢትዮጵያ ኦሮምያ ክልል በተወጠነው ግዙፍ የደን ልማት መርሃ ግብር እአአ እስከ 2030 በሚኖረው ጊዜ ውስጥ 4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ልቀት ለመቀነስ የሚደረጉ ጥረቶችን የሚደግፍ መሆኑ ታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG