በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቤት ሠራተኞችና አሰሪዎች ጉዳይ


የቤት ሠራተኞችና አሰሪዎች ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:01 0:00

መንግሥት የቤት ሠራተኞችና አሰሪዎች የሚዳኙበት የህግ ማዕቀፍ ሊያበጅ ይገባል ሲል "አንድነት" የተባለ ሃገር አቀፍ የቤት ሠራተኞች ማኅበር ጠየቀ።

በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ከፍቶ የሚንቀሳቀሰው እና ከ13ሺ በላይ አባላት እንዳሉት የገለፀው ማኅበሩ፣ በህግ ላይ የተመሰረተ የአሰሪና ሠራተኛ ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

የማኅበሩ ሊቀ መንበር ወ/ሮ ሂሩት፣ በቤት ሠራተኞችም ሆነ በአሰሪዎች ላይ የመብት ጥሰት የሚፈጸመው የኢትዮጵያ አሰሪና ሠራተኛ ሕጉ በውል ያስቀመጠው ነገር ባለመኖሩ ነው ብለዋል።

አሰሪዎች እና የህግ ባለሙያዎች በበኩላቸው “በቤት ሰራተኞች እና በአሰሪዎች ዙሪያ አሳሪ ህግ ባለመኖሩ እስከ ግድያ ድረስ የሚያደርሱ ከባድ ወንጀሎች እየተፈፀሙ በመሆኑ ሕግ አውጭው አካል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል” ይላሉ።

ጉዳዩ የሚመለከተው የፌዴራል ሥራና ክህሎት ሚንስቴርን የሥራ ኃላፊዎችን ለማነጋገር ከሁለት ሳምንት በላይ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG