በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ኮቪድ 19 የቲቢ በሽታ መከላከልን በአስርት ዓመታት ወደ ኋላ መልሶታል"


ዛሬ የዓለም የቲቢ ቀን ነው፡፡ ምስሉ የሚያሳየው እኤአ የካቲት 24 2018 ህንድ ውስጥ በሃይደባርድ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ አንድ የቤተሰብ አባል በትንፋሽ እጦት ለሚያጣጥር አንድ የቲቢ በሽተኛ የኦክሲጂን መውሰጃውን ሲያቀብል ነው፡፡ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስከፊውን የቲቢ በሽታ ለመከለከል አስቸኳይ የዘመቻ ጥሪ አስተላልፈዋል
ዛሬ የዓለም የቲቢ ቀን ነው፡፡ ምስሉ የሚያሳየው እኤአ የካቲት 24 2018 ህንድ ውስጥ በሃይደባርድ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ አንድ የቤተሰብ አባል በትንፋሽ እጦት ለሚያጣጥር አንድ የቲቢ በሽተኛ የኦክሲጂን መውሰጃውን ሲያቀብል ነው፡፡ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስከፊውን የቲቢ በሽታ ለመከለከል አስቸኳይ የዘመቻ ጥሪ አስተላልፈዋል

የዓለም ጤና ድርጅት የሳምባ ነቀርሳን (ቲቢን) ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ጨርሶ እየቀረ ነው ይላል፡፡ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ህይወት የሚቀጥፈውና ለዘመናት የቆየውን ይህን እድሜ ጠገብ በሽታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመግታት፣ አስቸኳይ እምርጃዎች መወሰድ ይኖርባቸዋል ሲልም አስጠንቅቋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የጤና ተቋም የዘንድሮውን የዓለም የቲቢ ቀን የሚያከብረው ይህንን ከባድ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት ጋር ነው፡፡

የዓለም መሪዎች በልማድ የሳንባ ነቀርሳ የሚባለውን ወይም ቲቢን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ያስቀመጡት ቀነ ገደብ ሊያልቅ አንድ ዓመት ቀርቶታል፡፡ አሁን 2022 ዓም እየተቃረበ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግን ያን ግብ ከፍጻሜ ማድረሱ የማይታሰብ መስሏል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ የቲቢ በሽታ አስመልከቶ የተቀናጀ ምርመራና ህክምና፣ እንዲሁም በሽታው ላለባቸው ሰዎች፣ ገና ከመነሻው ጀምሮ የሚያገኙትን እንክብካቤና ክትትል ለማድረግ፣ የታሰበውን ጥረት ሁሉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በእጅጉ እንደጎዳው፣ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣናት ያምናሉ፡፡

በዓለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ የሳንባ ነቀርሳ ፕሮግራም የሚሰሩ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ባለሙያ፣ የሆኑት ፍሊፕ ግላዙ፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የጤናና ማህበራዊ ሥርዐቶችን ያነጋ በመሆኑ ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቲቢን ለመቆጣጠር የተወሰዱ እምርጃዎችንም እንደጎዳው ተናግረዋል፡፡

84 በሚደርሱ አገሮች ውስጥ የሚገኙ፣ 1.4 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች፣ እኤአ 2020 መጀመሪያ ላይ ያገኙት የነበሩትን ህክምናና ክትትል ማጣታቸውንም ግላዙ ተናግረው የሚከተለውን አክለዋል፤

“ምንም ክትትል ሳይደረግበት የቆየ ቲቢ በሽታ 50 ከመቶ በላይ ለሆነው ሞት ምክንያት ይሆናል፡፡ የሳምባ ነቀርሳ በሽታ ካላቸው ሰዎች መካከል ተገቢው ክትትል ካልተደረገላቸው ግማሽ የሚደርሱት ሊሞቱ ይችላሉ፡፡ የተመጣጠነ የምግብ ችግርና የኤች አይቪ ቫይረሰ የተያዙ እንደሆነ ደግሞ የበለጡት ይሞታሉ፡፡ በቲቪ በሽታ ተያይዞ ከሚሞቱት ጋር ግማሽ ሚሊዮን ያህል ተጨማሪ ሰዎች በዚህ መንገድ እንደሚሞቱ ተረድተናል፡፡”

የቲቢ በሽታ፣ በመላው ዓለም፣ በገደይነታቸው ከሚታወቁት ተላላፊ በሽታዎች፣ ቀዳሚነቱን የሚይዝ ሲሆን፣ በዓመት 1.4 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን እንደሚገድል ተነግሯል፡፡

1.8 ቢሊዮን የሚደርሱና የዓለምን አንድ አራተኛ መጠን ያላቸው ሰዎች ደግሞ፣ በሽታውን በሚያሲዘው ባክቴሪያ ወይም ተዋህስ የተበከሉ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ኮቪድ 19 የቲቢ በሽታ መከላከልን በአስርት ዓመታት ወደ ኋላ መልሶታል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:22 0:00


ከኮቪድ19 ወረርሽኝ በፊት የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚገምተው፣ በዓመት ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በበሽታው ይያዛሉ፡፡ የጤና ድርጅቱ ዓለም አቀፍ የቲቢ በሽታዎች ፕሮግራም መሪ፣ ተሬዛ ካሴቫ እንደሚሉት፣ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት መደበኛውን የቲቢ ምርመራ የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል፡፡ ያ ማለት ግን በበሽታው ያለባቸው ሰዎች ቁጥርን ያመለክታል ማለት አይደለም፡፡

እሳቸው እንደሚሉት እኤአ በ2020 ዓመት ብቻ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆኑ ሰዎች ተገቢውን ህክምና ባለማግኘታቸው በቲቢ በሽታ ሳይሞቱ እንዳልቀሩ በመገመት፣ የዓለም ጤና ድርጅትን ያሳሰበው መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ስለሆነም የተቀናጀ ምርመራ አስፈላጊ መሆኑን ካሴቫ እንዲህ በማለት ይናገራሉ

“የተናቀጀ የቲቢ ምርመራ ማድረግ በበሽታው የተያዙትንም ሆነ ለበሽታው የተጋለጡትን ሰዎች ይበልጥ ለመርዳትና ለመካለል ያስችላል፡፡ በተቀናጀ መንገድ የምናካሂደው የቲቢ ምርመራ በሽታው ገና ከመነሻው ልንደርስበት ያስችለናል፡፡ ሰዎችም ከምርመራው ተጠቃሚ በመሆን በሽታውን ቶሎ አውቀው እንዲከላከሉት ያስችላቸዋል፡፡”

የዓለም ጤና ድርጅት እንዳሳታወቀው እኤአ፣ በ2019 ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የቲቢ በሽታን አስመልከቶ የመከላከያውንም ሆነ የእንክብካቤውን ህክምና ያገኙት ሰዎች ቁጥር በ20 ከመቶ ቀንሷል፡፡

ክፍተቱ በትልቁ ከታየባቸው አገሮች መካከልም ኢንዶኔዥያ ደቡብ አፍሪካ ፊልፒንስ እና ህንድ እንደሚገኙበት የጤና ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

የቪኦኤ ዘጋቢ ሊሳ ሽላይን ከጄኔቭ ከላከችው ዘገባ የተወሰደ፡፡

XS
SM
MD
LG