በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወላይታ ዞን የጋራ ክልል ጥያቄ ውሳኔ-ሕዝብ-ምርጫ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ተካሔደ


የወላይታ ዞን የጋራ ክልል ጥያቄ ውሳኔ-ሕዝብ-ምርጫ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ተካሔደ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:13 0:00

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በዛሬው ዕለት የተካሔደው የውሳኔ ሕዝብ ምርጫ፣ በደቡብ ክልል የሚገኙ ስድስት ዞኖችንና አምስት ልዩ ወረዳዎችን፣ የጋራ ክልል ጥያቄ ውሳኔ ሕዝብ አካል ነው፡፡

ባለፈው ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ተከናውኖ የነበረው የምርጫ ውጤት፣ በሕግ ጥሰት ምክንያት በመሰረዙ፣ ውሳኔ ሕዝቡን በድጋሚ ማካሔድ እንዳስፈለገ ተገልጿል።

የአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው፣ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር፣ አማካሪ፣ ጠበቃ እና በዩኒቨርሲቲው የሕግ ክፍል የምርምር እና ማኅበረሰብ አገልግሎት ተባባሪ ፕሮፌሰር ነቢዩ ማርቆስ፣ የቀረቡ አማራጮች፥ ግልጽነት የጎደላቸው እና በመራጩ ዘንድ ብዥታን የሚፈጥሩ እንደኾኑ ይተቻሉ፡፡ መምህሩ እንደተናገሩት፣ በውሳኔ ሕዝቡ፣ “ከሌሎች ጋራ አልደራጅም” የሚል አማራጭ

ብልጫ ቢያገኝም፣ “ለብቻዬ መደራጀት እፈልጋለኹ” የሚል አማራጭ ስለሌለው፣ ለሌላ ውሳኔ ሕዝብ የሚጋብዝ ነው፤ ሲሉ፣ ጉድለት ያሉትን አስረድተዋል።

ወደ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ያቀናው፣ የሐዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ፣ የመራጮችን አስተያያት አካትቶ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG