በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባንተኛስ?!


ባንተኛስ?!
please wait
Embed

No media source currently available

0:00 0:33:49 0:00

ባንተኛስ?!

ለሕይወት እጅግ አስፈላጊ የኾነው እንቅልፍ፣ ከዕድሜ ዘመናችን ሲሶውን እንደሚወስድና ያን ያህሉን መዋዕለ ዘመን ሊሸፍን እንደሚገባው፣ የሥነ አእምሮ ጠቢባን ይናገራሉ፤ ይመክራሉም።

የእንቅልፍ ሰዓትን በወጥነት ጠብቆ በአግባቡ መተኛት ያለውን ጥቅም ያህል፣ የሰው ልጅ መተኛት በሚገባው ጊዜ እና መጠን አለመተኛቱ ያለው መዘዝም፣ እጅግ የከፋ እንደኾነ፣ ባለሞያዎች ይናገራሉ።

የአንጎል መጠን መቀጭጭ፣ በወንዶች ዘንድ የዘር ሕዋሳት አመንጪ ፍሬዎች መሟሸሽ፣ በሴቶች ደግሞ የሰውነት ውስጥ የተፈጥሮ ቅመሞች መዛባት… ወዘተ. የእንቅልፍ ዕጦት እና መዛባት ሊያስከትላቸው ከሚችላቸው፣ የበዙ የጤና መስተጓጎል መገለጫዎች፣ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።

በጉዳዩ ላይ የተያዘው ቅንብር እና ውይይት፣ በርካታ ቁም ነገር ያስጨብጡዎታል፤ ይከታተሉት፡፡

XS
SM
MD
LG