ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ውስጥ ተከስቶ በነበረው የኢቦላ ወረርሽኝ ወቅት በዚያ ይሰሩ የነበሩ አንዳንድ የዓለም የጤና ድርጅት ሰራተኞች “ሴቶች ላይ የወሲባዊ በደል እና ብዝበዛ አድራጎት ፈጽመዋል” የሚሉ ውንጀላዎች ቀርበውባቸዋል፡፡
አሶስየትድ ፕሬስ ከለንደን ያጠናቀረው ዘገባ ጨምሮ እንዳመለከተው፡ ውንጀላውን በሚመለከት ምርመራ እንዲያካሂዱ ድርጅቱ ራሱ የሰየማቸው ባለሙያዎች ባወጡት መግለጫ “ተቋሙ ጉዳዩን በተገቢው መንገድ አልያዘውም፡፡”