በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአሥር ዘጠኙ የዓለማችን ሕዝብ የተበከለ አየር ይተነፍሳል


ከአሥር ዘጠኙ የዓለማችን ሕዝብ የተበከለ አየር ይተነፍሳል
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:59 0:00

ከአሥር ዘጠኙ የዓለማችን ሕዝብ የተበከለ አየር ይተነፍሳል

የቤት ውስጥ አየር ብክለት ከፍተኛና ዋናው በውል ያልታወቀ ችግር መሆኑን የገለጸው የዓለም ጤና ድርጅት/WHO/ ከአሥር፣ ዘጠኙ የዓለማችን ሕዝብ የተበከለ አየር እንደሚተነፍስ አስታወቀ።

የቤት ውስጥ አየር ብክለት ከፍተኛና ዋናው በውል ያልታወቀ ችግር መሆኑን የገለጸው የዓለም ጤና ድርጅት/WHO/ ከአሥር፣ ዘጠኙ የዓለማችን ሕዝብ የተበከለ አየር እንደሚተነፍስ አስታወቀ።

በቅርቡ ይፋ የሆነው የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት በሰጠው መግለጫ፣ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ፣ በአየር ብክለት ሕይወቱ እንደሚያልፍ ገልጧል። በዚህም ዋናዎቹ ሰለባዎች አፍሪካና እስያ መሆናቸው ተመልክቷል።

የድርጅቱ የሕዝብ ጤና ጥበቃና ማህበራዊ አገልግሎት ዶ/ር ማሪያ ናይራ እንዳብራሩት፣ በግምት ሰባት ሚሊዮን ሰዎች በአየር ብክለት ሕይወታቸውን ያጣሉ። ከቤት ውጪ ባለ ብክለት 4.2 ሚሊዮን ሕዝብ ይሞታል። ወደ 3.8 ሚሊዮን የሚሆኑ ደግሞ በተበከለ ጋዝ ምግብ የሚያበስሉና በሌላ የቤት ውስጥ ባለአገልግሎት የሚጠቀሙ ናቸው።

ዶ/ር ነይራ እንደገለጹት፣ የዓለም ጤና ድርጅት/WHO/ በመጪው ጥቅምት ወር ጄኔቫ ላይ መፍትሔ የሚሻ አንድ ዓለማቀፍ የአየር ብክለት ጉባዔ ይጠራል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG