በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮቪድ-19 የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እንደሚጨምር ተጠቆመ


በመጪዎቹ ጥቅምትና ኅዳር ወራት በኮቪድ-19 ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ይጨምራል ብለው እንደሚገምቱ የዓለም የጤና ድርጅት የአውሮፓ ቅርንጫፍ ኃላፊው ተናገሩ።

ሃንስ ክሉገ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት ቃል "እየከፋ ነው የሚሄደው፣ ጥቅምት እና ኅዳር ውስጥ ብዙ ሰው ይሞታል ብለን እንሰጋለን” ብለዋል።

የኮቪድ-19 ክትባት ቢገኝ እንኳን ዓለምቀፉ ወረርሽኝ አበቃ ማለት እንደማይሆንም አሳስበዋል።

"የሚገኘው ክትባት ለሁሉም ህዝብ የሚሆን ወይም ሁሉንም የሚረዳ እንደሚሆን አናውቅም። የተወሰነ የህዝብ ክፍል ቫይረሱን እንዲከላከል እንደሚረዳ ለሌላው ደግሞ ምንም ላይጠቅም እንደሚችል ከወዲሁ ፍንጮች እያገኘን ነው፤ ያ ከሆነ ደግሞ የተለያዩ የክትባት ዓይነቶችን ማዘዝ ሊኖርብን ነው፤ እንደዚያ ሲሆን የሚኖረውን የማጓጓዣና የማከፋፈል መከራ ማየት ነው" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG