ዋሺንግተን ዲሲ —
በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማፅያን በዚህ ሳምንት በሳውዲ አረቢያ ንጉሣዊ ቤት መንግሥት ላይ በተወንጫፊ ሚሳይል ያደረሱትን ጥቃት ዋይት ኃውስ አጥብቆ አወገዘ።
ዩናይትድ ስቴትስ ይህ የኋለኛው የሚሳይል ጥቃቱ ዒላማ ያደረገው የሳውዲ ንጉሥ ሳልማን ቢን አብደላዚዝ ቢን ሳልማንን መኖሪያ ቤተ መንግሥትን መሆኑን አመልክታለች።
ትናንት ሃሙስ የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ሣራ ሃከቢ ሳንደርስ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢራንን የፀጥታ ጥበቃው ምክር ቤት የመንን አስመልክቶ ያስተላለፈውን ውሳኔ በመጣስዋ በተጠያቂነት እንዲይዛት አሳስበዋል።
ኢራን ሁቲዎቹን ታስታጥቃለች መባልዋን እንጂ መርዳቱዋን አታስተባብልም፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ