በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 25 ኤርትራዊያን እና 12 ኢትዮጵያዊያን ጣልያን ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ


ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ 25 ኤርትራዊያን እና 12 ኢትዮጵያዊያን ጣልያን ውስጥ በተካሄደ አሰሳ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።

የጣልያን የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው መልእክት በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ይሠራ የነበረው አደገኛ የወንጀለኞች መረብ ከሥራ ውጭ ሆኗል ብለዋል።

ሰዎቹ የታሠሩትም ሮም ከተማ ውስጥ በተካሄደ አሰሳ ሲሆን አሰሳው የተካሄደው በ2014ዓ.ም ከህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሥራ ጋር በተያያዘ ሲሲሊ ውስጥ በቁጥጥር ሥር የዋለው የ32 ዓመት ኤርትራዊ ለፖሊስ በሰጠው መረጃ መሰረት መሆኑን የጣልያን ፖሊስ ገልጿል።

“ከፖሊስ ጋር ለመተባበር የወሰንኩበት ምክንያት በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በጉዞው በመሞታቸው ነው”ሲል ቃሉን ለፖሊስ ሰጥቷል።

በተጨማሪም ግለሰቡ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይህን ሜዲተራንያን ባህር ለመሻገር በሚካሄድ አደገኛ ጉዞ ይሞታሉ እነዚህ ደግሞ ከጠቅላላ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሂደት ከሚሞቱት የተወሰነወን ቁጥር ነው ብሏል።

የጣልያን ባለሥልጣናት ለመጀመርያ ጊዜ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር በሰሜን አፍሪካ፡ጣልያንና ሌሎች የአውሮፓ አገሮች ላይ የሚሠሩ ሰዎች ዝርዝር መረጃ ለማግኘት መቻሉን አስታውቋል።

ይህ ኤርትራዊ ግለሰብ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የሚሠሩ በቂ ገንዘብ የሌላቸውን ስደተኖችን ለመግደል ወደ ኋላ እንደማይሉ በመግለጽ፤ ጉዟቸውን ለመቀጠል አካላቸውን ለግብጻዊያን ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ለመሸጥ እንደሚገደዱ እንዲሁም እጅግ በጣም ዘግናኝ ድርጊቶች እንደሚካሄዱ ለሃገሪቱ ባለሥልጣናት አስረድቷል።

የጣልያን ባለሥልጣናት ከግለሰቡ ባገኙት መረጃ መሠረት ይህ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሥራ የተሰማራ መረብ በአፍሪካ ቀንድ የሚበቅለው የጫት እጽ ንግድ ላይና የውሸት ቃል-ኪዳን ለስደተኞች በማዘጋጀት የመሳሰሉ ሌሎች ወንጀሎች ላይም የተሠማራ መሆኑን አስረድቷል።

የጣልያን ፖሊስ ባለፈው ወር ባካሄደው አሰሳ በቡድኑ እንቅስቃሴ ዝርዝር መረጃ እና 526,000 ዩሮ እና 25,000 የአሜሪካ ጥሬ ገንዘብ ማግኘቱን አስታውቋል።

በተመድ የስደተኞች ተቋም ሪፖርት መሠረት አውሮጳ ከሁለተኛ የአለም ጦርነት በኃላ ያጋጠማት ትልቁ የስደተኞች ቀውስ ሲሆን ከ2014 ዓ.ም እስካሁን አውሮፓ ለመድረስ በሚካሄደው ጉዞ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 10,000 መድረሱን እና በዚህ በያዝነው የአውሮጳዊያን ዓመት ብቻ 2,800 ሰዎች መሞታቸውን ተቋሙ ያስረዳል።

የባልካን ሀገሮች መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ይህን አደገኛ የሜዲተራንያን ባህር ጉዞ በማቋረጥ ጣልያን የሚደርሱ የስደተኞች ቁጥር ከፍ ማለቱን ተቋሙ አስረድቷል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ቀጥተኛ መገናኛ

ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 25 ኤርትራዊያን እና 12 ኢትዮጵያዊያን ጣልያን ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:43 0:00

XS
SM
MD
LG