ባለፈው ሳምንት የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ 165 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል መድረሳቸውንና 94 ተሽከርካሪዎች ደግሞ በጉዞ ላይ መሆናቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታውቋል። የድርጅቱን መረጃ ያረጋገጡት የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ፣ ከዚህም ውጭ በአየር እና በየብስ የሚደረገው የእርዳታ አቅርቦት መቀጠሉን አብራርተዋል፡፡ይሁንእንጂ ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ያለው የዕርዳታ አቅርቦት ከሚያስፈልገው አንጻር እጅግ አነስተኛ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት ሞትና ረሃብ እየተስፋፋ እንደሚገኝ የትግራይ ክልል የግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ መሆናቸውን የገለጹት ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ፣ በቅርቡ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡ ወደ ክልሉ ለሚደረገው የዕርዳታ አቅርቦት ማነስ የትግራይ ክልል አመራሮች እና አንዳንድ የረድኤት ድርጅቶች መንግስትን ተጠያቂ ቢያደርጉም፣ መንግሥት ግን ውንጀላውን አይቀበልም፡፡
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ሜይ 17, 2022
ዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ሥምምነት ከኢትዮጵያ ጋር ተፈራረመ
-
ሜይ 17, 2022
የደራሼ ግጭት በመባባሱ መንገድ መዘጋቱን ነዋሪዎች እና አሽከርካሪዎች ገለፁ
-
ሜይ 17, 2022
የሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት እና አንድምታው
-
ሜይ 16, 2022
የኢትዮጵያው ተደጋጋሚ ድርቅ የአየር ንብረት ለውጡ ማሳያ ነው