በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምግብ ድርጅቱ በትግራይ 1 ሚሊዮን ተረጂዎችን ረድቻለሁ አለ


የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት፣ በሰሜን ምዕራብና ደቡብ ትግራይ ዞኖች የምግብ እርዳታውን ማከፋፈል ከመጀመረበት ካለፈው መጋቢት ወር አስንቶ ፣ ወደ 1 ሚሊዮን ለሚጠጉ ተረጅዎች እርዳታ ማድረጉን በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በተነሳው ግጭት 91 ከመቶ የሚሆነው 5.2 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን የምግብ ድርጅቱ ገልጾ፣ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የአገልግሎቱን መጠን እያሰፋ እስከ 70 ወረዳዎች ድረስ የሚገኙት ተረጅዎች ዘንድ ለመድረስ በማቀድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም በመግለጫው አመልክቷል፡፡

በመግለጫው እንደተመተለከተው “አስቴር በየነ የ43 አመት ሴት ሲሆኑ፣ የሰባት ልጆች እናት ናቸው፡፡ በግጭቱ ሳቢያ ከሁለት ወር በፊት ቤታቸውንና ሰብላቸውን አጥተዋል፡፡ በዚህ የተነሳም አንድ ሚሊዮን ከሚቆጠሩት ተረጅዎች መካከል አንዷ በመሆን ከዓለም አቀፉ የምግብ ድርጅት የአተርና የአትክልክት ዘይት እርዳታ ተካፋይ ሆነዋል፡፡”

ከሰሜን ምዕራብ ትግራይ ከምትገኘው ሽሬ፣ 50 ኪሎሜተር ርቀት ላይ በምትገኘዋ አዲ ሚለን፣ ነዋሪ የሆኑት አስቴር፣ “እስካሁን ድረስ ያለነው፣ ከጎረቤታችን በማገኘው አነስተኛ የምግብ እርዳታ ነበር፡፡ አሁን ግን ቢያንስ ከሚያሰቃየን ረሀብ የሚያስታግሰን እርዳታ እያገኝን ነው፡፡” ማለታቸውን መግለጫው ጠቅሷል፡፡ የዓለም ምግብ ድርጅት፣ ወደ 4ሺ500 ለሚገኙ የመንደሪቱ ነዋሪዎች፣ ትግራይ ውስጥ በየስድስት ሳምንቱ አንዴ የሚታደለውን የመጀመሪያውን ዙር የምግብ እርዳታ እያከፋፈለ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

አስቴር ጨምረው ሲናገሩ” የዓለም ምግብ ድርጅት ከብዙ ከተሞችና ገበያዎች ተቆራርጠንና ርቀን በምንግኘበት አዲ ሚለን ድረስ የምግብ እርዳታ ሊያመጡልን በመቻላቸው ተደስቻለሁ” ማለታቸው ተመልክቷል፡፡

የዓለም የምግብ ድርጅት በትግራይ ሰሜን ምዕራብና ደቡብ ዞኖች አስቸኳይ የምግብ እርዳታዎችን የማቅረብ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ገልጾ፣ በአካባቢውም እርዳታውን ከፍ በማድረግ 2.1 ሚሊዮን ለሚደርሱ ሰዎች ለማዳረስ ማቀዱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ካለፈው ሚያዝያ ጀምሮ በሰሜን ምዕራብ 13ወረዳዎችን በማዳረስ ለ885ሺ ሰዎች እርዳታውን ማቅረብ መቻሉንም ገልጿል፡፡ ካለፈው መጋቢት ጀምሮ በደቡባዊ ትግራይ ወረዳዎች የሚገኙ 168ሺ ሰዎች የዓለም ምግብ ድርጅት የሰጠውን እርዳታ በመቀበላቸው እስካሁን እርዳታውን ያገኙ ሰዎች ቁጥር 1.5 ሚሊዮን እንዲደርስ ማድረጉንም ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

ድርጅቱ ወደ ሰሜን ምዕራብና ደቡብ ትግራይ እንዲሰማራ ከመደረጉ በፊት በምስራቅ ትግራይ ለ33ሺ ለሚደርሱ ሰዎች እርዳታውን ማከፋፈሉን አስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅቱ በየስድስት ሳምንቱ አንዴ በሚሰጠው የምግብ እርዳታ፣ መርሃ ግብር መሰረት፣ በዚህ ሳምንት ሁለተኛውን ዙር እርዳታ መስጠት ጀመሩን ገልጿል፡፡ ወደ ድርጅቱ ሥራ እንዲካተቱ ከተደረጉ ከአምስቱ አዳዲስ ወረዳዎች በሁለቱ የኮረምና ኦፍላ ወረዳዎች ሁለተኛ ዙር መጀመሩን ጠቅሷል፡፡

እንቅስቃሴዎቹ በተጀመሩባቸው ጥቂት ቀናት ውስጥ ሊረዳ ካቀዳቸው 200ሺ ተረጅዎች መካከል 80ሺዎቹን ይሸፍናል ተብሎ እንደሚጠበቅም ድርጅቱ አስገንዝቧል፡፡

የምግብ ድርጅቱ፣ በመላው ትግራይ የሚደረገውን የአስቸኳይ የተመጣጠነ ምግብ እርዳታ እንቅስቃሴን፣ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ሆኖ የሚመራ መሆኑን አስታውቆ፣ እስከ 70 ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ተረጅዎች ዘንድ ለመድረስ በማቀድ፣ የአገልግሎት መጠኑን እያሰፋ መሆኑን አመልክቷል፡፡

በተለይም በገጠር አካባቢዎች የሚገኙት ዘንድ ያለው ተደራሽነት ግን አሁንም ዋነኛ ችግር መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

የምግብ ድርጅቱ በትግራይ 1 ሚሊዮን ተረጂዎችን ረድቻለሁ አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:41 0:00

የዓለም ምግብ ድርጅት ካለፈውመጋቢት ወር ጀምሮ ከምዕራብ ትግራይ በስተቀር በ31 ወረዳዎች ውስጥ 315 ሺ አስቸኳይ አልሚ ምግቦችን፣ ወደ 100ሺ ለሚጠጉ ህጻናት እርጉዝና በእንክብካቤ ላይ ላሉ ሴቶች እንዲዳረስ ማድረጉን አስረድቷል፡፡

ለሰአብአዊ ድጋፍ በሚሰጠው አጠቃላይ ምላሽ መሰረት የዓለም ምግብ ድርጅት 40ሺ ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ የምግብ እርዳታን ለመንግሥትና ለአጋሮች በኩል ወደ ትግራይ ያዳረሰ መሆኑን፣ እንዲሁም 22ሺ ሜትሪክ ቶን በክልሉ ውስጥ ለሚገኘው ለብሄራዊ አደጋና ስጋት አስተዳደር ኮሚሽን ማጓጓዙን ዘርዝሮ ጠቅሷል፡፡

ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በተነሳው ግጭት 91 ከመቶ የሚሆነው 5.2 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ አስሸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን ዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅቱ አመልከቷል፡፡

“የተናቀጀ የምግብ ዋስትና ደረጃዎችን የሚያመላከተው ድርጅት ((IPC) በትግራይ ያለውን የረሀብ መጠን በሚመለከት፣ ከሚያወጣው የዘገባ ውጤት በፊት፣ የአለም አቀፉ የምግብ ድርጅት በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ፣ በትግራይ የተመጣጠነና አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብለን የምናስባቸው ሰዎች ቁጥር፣ እስከ 2.1 ሚሊዮን ይደርሳል ብለን እንሰጋለን” ሲል ባወጣው መግለጫ አመልከቷል፡፡

የዓለም የምግብ ድርጅት በትግራይ ያለውን የምግብ እርዳታ አቅርቦቱን እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በቀጣይነት ለማስፋፋት 203 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG