በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ በኦሮሞ ነፃነት ታጣቂቾ ተፈፀመ በተባለ ጥቃት ሁለት ሰዎች ትላንት መገደላቸውን ነዋሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
የኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ሰላም እና ፀጥታ ጽህፈት ቤት፣ በግብርና ሥራ ላይ ነበሩ ያላቸው ሁለት ሲቪሎች ከኦሮሚያ ክልል ምእራብ ጉጂ ዞን ወሰን የተሻገሩ በተባሉ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታውቋል።
በጥቃቱ ከተጎዱት መካከል አንደኛው እዛው የተመታበት ሲሞት፣ ሁለተኛ ደግሞ ወደ ኬሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ መሞቱን ሆስፒታሉ አረጋግጧል።
በግድያው ስሙ ተነስቶ ከተወነጀለው ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቃለአቀባይ አቶ ጅረኛ ጉዴታ ምላሽ ለማካተት ያደርግነው ጥረት አልተሳካም።
መድረክ / ፎረም