በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

1ሺሕ500 ስደተኞች ወደ አፍጥጥ መጠለያ መዛወራቸው ተገለጸ


please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00

በምዕራብ ጎንደር ዞን ከሚገኙት የአውላላ እና ኩመር መጠለያዎች፣ 1ሺሕ500 ስደተኞች ወደ ዐዲሱ የአፍጥጥ መጠለያ መዛወራቸውን የመተማ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ሞገስ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ከአውላላ መጠለያ ወጥተው መኖሪያቸውን በጎዳና ዳር ያደረጉትን የሱዳን ስደተኞችንም፣ “ወደ ዐዲሱ መጠለያ እንዲዛወሩ የማግባባት ሥራ እየተከናወነ ነው፤” ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር በምኅጻሩ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር፣ በዚኽ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ በላከው ኢሜይል፣ የጸጥታ ችግር አለባቸው በሚባሉት የአውላላ እና የኩመር መጠለያዎች የሚገኙትን ኹሉንም ስደተኞች ወደ አፍጥጥ ለማዛወር ማቀዱን ገልጿል።

የስደተኞቹን ዝውውር በማስመልከት ዛሬ ዐርብ መግለጫ ያወጣው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም፣ ውሳኔውን እንደሚያደንቅ ገልጾ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በመጠለያዎች አካባቢ ያለውን የጸጥታ ኹኔታ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርቧል።

XS
SM
MD
LG