በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዌንዲ ሸርማን ኢትዮጵያን በዴሞክራሲ ሃገርነት አሞገሱ፤ ተቃውሞዎች ገጥመዋቸዋል


ዌንዲ ሸርማን - የአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ዌንዲ ሸርማን - የአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ኢትዮጵያ ነፃና ፍትሐዊ እንደሚሆን የሚጠበቀውን ምርጫ እያካሄደች ያለች ዴሞክራሲያዊ ሃገር ነች ሲሉ የአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዌንዲ ሸርማን ተናገሩ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:12:27 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኢትዮጵያ ነፃና ፍትሐዊ እንደሚሆን የሚጠበቀውን ምርጫ እያካሄደች ያለች ዴሞክራሲያዊ ሃገር ነች ሲሉ የአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዌንዲ ሸርማን ተናገሩ፡፡

የአንጋፋው ተቃዋሚ ፓርቲ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ግን የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ በ1983 ዓ.ም ወደነበረበት ተመልሷል ብለዋል፡፡

የቀድሞው ግንቦት ሰባት መሪ የነበሩት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ደግሞ “…ሚስ ሸርማን እራሣቸው የሚሠሩበት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሚያወጣው ዓመታዊ ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግሥት እራሡ ያወጣውን ሕግ የማያከብር፤ ለምንም ዓይነት ዴሞክራሲያዊ እሴቶች ደንታ የሌለው፣ ሥርዓቱን የተቃወመ ማንንም አሸባሪ እያለ የሚያስር መሆኑን በተደጋጋሚ እንደሚናገር…” አመልክተዋል፡፡

የፍሪደም ሃውስ የአፍሪካ ፕሮግራም ኃላፊ ቢከቪን ፒትሮቪች በሰጡት መግለጫ “የረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዌንዲ ሸርማን መግለጫ ያላዋቂ ንግግርና ጥቅምም የሌለው ነው” ብለዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG