በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ራያ ቆቦ ወረዳዎች ውስጥ የተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ነዋሪዎችን ማፈናቀሉ ተገለፀ


ራያ ቆቦ ወረዳዎች ውስጥ የተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ነዋሪዎችን ማፈናቀሉ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:16 0:00

አማራ እና ትግራይ ክልልን በሚያዋስኑ የሰሜን ወሎራያ ቆቦወረዳዎች ውስጥ የህወሓት ታጣቂዎች፣ “ፋኖ” የሚል መጠሪያ ካለው ታጣቂዎች ጋር ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለፁ።

ነዋሪዎቹ “በአካባቢው የተካሄደው ውጊያ ነው” ብለውታል። ውጊያውን ተከትሎም የህወሓት ታጣቂዎች አራት ጎጦችን መቆጣጠራቸውን ተናግረዋል።

ጃሮታ፣ አረንገቦና አዲሱ ሰፈር ከተባሉ የወረዳው አካባቢዎችም ከ160 የሚበልጡ ሰዎች ተፈናቅለው ወደ አቅራቢያቸው የሚገኙ አካባቢዎች መሸሻቸውን ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ወደ ትግራይ ክልል ደውለን መረጃ ለማግኘት የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለመኖር ምክንያት እስካሁን ከህወሓት በኩል በጉዳዩ ላይ ምላሽ አላገኘንም። ምላሽ እንዳገኘን ይዘን እንመለሳለን።

XS
SM
MD
LG