የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሄሪስ፣ በመጪው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በእጩ በምክትል ፕሬዝደንትነት ከጎናቸው ሆኖ የሚወዳደረውን ግለሰብ ለመምረጥ ተቃርበዋል። የሚመረጡት እጩም ነገ ማክሰኞ ካመላ ሄሪስ በፔንስልቬኒያ በሚያደርጉት የምርጫ ዘመቻ ላይ አብረዋቸው ይሆናሉ ተብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ፣ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ቀጣዩ ፕሬዝደንታዊ የምርጫ ክርክር የሚካሄድበት መድረክ እንዲቀየር ጥሪያቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ አቅርበዋል።
ቬሮኒካ ባልዴራስ ኢግሌሲያስ ዝርዝሩን ልካለች፡፡