በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የነፃነት ደወል ያስተጋባ - ሃምሣ ዓመት ተከበረ

OBAMA, MLK
OBAMA, MLK

የዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከሲቪል መብቶች ትግል ፋና ወጊዎችና አራማጆች ጋር ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ ላይ ለክብረ በዓል ወጥተው ዋሉ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:11:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

/ከግራ ወደቀኝ፤ ቢል ክሊንተን፣ ኦፕራ ዊንፍሬ፣ ሚሸል ኦባማ፣ ካሮላይን ኬኔዲ፣ ባራክ ኦባማ/ - ነኀሴ 22/2005 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲ.ሲ - ሊንከን መታሰቢያ
/ከግራ ወደቀኝ፤ ቢል ክሊንተን፣ ኦፕራ ዊንፍሬ፣ ሚሸል ኦባማ፣ ካሮላይን ኬኔዲ፣ ባራክ ኦባማ/ - ነኀሴ 22/2005 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲ.ሲ - ሊንከን መታሰቢያ

የዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከሲቪል መብቶች ትግል ፋና ወጊዎችና አራማጆች ጋር ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ ላይ ለክብረ በዓል ወጥተው ዋሉ፡፡

ዕለቱ፣ ነሐሴ 22/1963 ዓ.ም የዋሽንግተን ሰልፍ እየተባለ የሚጠራው በመብቶች ታጋዩ ማርቲን ሉተር ኪንግ ዳግማዊ የተመራው የሥራና የነፃነት ሰልፍ የተካሄደበት ነው፡፡

በዚያ ልክ ዛሬ ሃምሣ ዓመቱን በደፈነው ሰልፍ ላይ ከሁለት መቶ ሃምሣ ሺህ በላይ ሰው ተገኝቶ ነበር፡፡

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ያኔ ማርቲን ሉተር ኪንግ ቆመው “ይታየኛል” (አይ ሃቭ ኧ ድሪም) ንግግራቸውን ያደረጉበት ቦታ ላይ ቆመው ለመታሰቢያው ያዘጋጁትን ንግግር አድርገዋል፡፡
የዋሽንግተን ሰልፍ ሃምሣኛ ዓመት ሲከበር - ረቡዕ፤ ነኀሴ 22/2005 ዓ.ም - ዋሽንግተን ዲ.ሲ - ብሔራዊ አደባባይ
የዋሽንግተን ሰልፍ ሃምሣኛ ዓመት ሲከበር - ረቡዕ፤ ነኀሴ 22/2005 ዓ.ም - ዋሽንግተን ዲ.ሲ - ብሔራዊ አደባባይ

“ኪንግ ለሚሊዮኖች ድምፅ አልባ ተስፋዎች እጅግ የገነነ ድምፅ ሆኑ” ሲሉ በሥፍራው ለታደሙ በሺሆች የሚቆጠሩ የሁሉም ቀለሞች ሰዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ለዛሬው ዕለት ያበቁን ያሏቸውን “ያልተፈከረላቸው ጀግኖች”ም ከፍ አድርገው አሞግሰዋል፡፡

በዛሬው ሥነ-ሥርዓት ላይ የቀድሞዎቹ ፕሬዚዳንቶች ጂሚ ካርተር እና ቢል ክሊንተን፣ እንዲሁም የዶ/ር ኪንግ ልጆችና ቤተሰቦች ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡

የልጃቸው ልጅም በሊንከን ማታሰቢያ ላይ የቆመውን “የነፃነት ደወል” ደውላለች፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG