በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምሕርት ቤቶችን ለመመለስ ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ይፈጃል ተባለ


በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምሕርት ቤቶችን ለመመለስ ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ይፈጃል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:08 0:00

በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት እስካሁን አራት ሺህ አንድ መቶ ሰባት ትምህርት ቤቶች ውድመት እንደደረሰባቸውና ወደ 19 ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎች ደግሞ ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።

የወደሙትን ትምሕርት ቤቶች ለመመለስም ከ11 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚፈጅ ቢሮው ጨምሮ ገልጿል። ህወሃት ለሁለት ሳምንት ተቆጣጥሮት በነበረው ሸዋሮቢት ከተማ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እና ወላጆችም ጦርነቱ ባደረሰው ከፍተኛ ውድመት ምክንያት ወላጆች ከሀብት ንብረታቸውን በማጣታቸውና በከተማው የሚገኙ ሁሉም ትምሕርት ቤቶች ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ለከፍተኛ የሥነ ልቦና ችግር መጋለጣቸውን ገልፀዋል።
XS
SM
MD
LG