በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ አክሲዮን ገበያዎች አሽቆልቁለው አደሩ


እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በኒው ዮርክ አክስዮን ገበያ
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በኒው ዮርክ አክስዮን ገበያ

በአሜሪካ የሚገኙ ሦስቱም ዋና የአክሲዮን ገበያዎች ትላንት ሰኞ በከፍተኛ ደረጃ አሽቆልቁለው አድረዋል። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በአሜሪካ የንግድ ሸሪኮች ላይ በጣሉት ታሪፍ እንዲሁም በሚቀጥሉት ወራት ኢኮኖሚው እንደማይዳከም ማስተማመኛ አለመስጥታቸው ኢንቨስተሮችን ያሳሰበ ጉዳይ ሆኗል።

በዳው ጆንስ የአክሲዮን ገበያ የነበሩ 30 ብሉ ቺፕስ አክሲዮኖች በ2.1 በመቶ ሲያሽቆለቁሉ፣ የስታንዳርድ ኤንድ ፑር 500 (ኤስ ኤንድ ፒ 500) ደግሞ በ2.7 በመቶ ወርዷል። በአብዛኛው ቴክኖሎጂ ነክ አክሲዮኖችን የያዘው ናስዳክ ደግሞ በ4 በመቶ ዝቅ ብሏል።

ኤስ ኤንድ ፒ 500 ከአንድ ወር በፊት ከነበረበት ከፍተኛ ሽያጭ በ8.6 በመቶ ወርዷል። ናስዳክ ደግሞ ከመስከረም 2014 ዓ/ም ወዲህ በአንድ ቀን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ሲያሽቆለቁል ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የትረምፕ ታሪፍ መጫን ኢንቨስተሮችን ስጋት ውስት ጥሏል።

የንግድ ምኒስትሩ በአሜሪካ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል እንደማይኖር ቢናገሩም፣ ትረምፕ ግን “መተንበይ አልወድም፣ ነገር ግን የሽግግር ወቅት ይኖራል።“ ብለዋል

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG