በዋልድባ ገዳም ይዞታ ላይ የስኳር ፋብሪካ ሊገነባ ነው በመባሉ ዕቅዱን በመቃወም ከጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች እሥፍራው ድረስ ሄደው በመሰባሰብ ሥራውን ከሚያካሂዱ ሠራተኞች ጋር ፍጥጫ ላይ መሆናቸውን ትናንት ከምንጮቻችን ያገኘንውን ማስተላለፋችን ይታወሳል።
ለጥበቃ የተሠማሩ ወታደሮች በሕዝቡ ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳይወስዱም መንግሥት ማስጠንቀቁንም እኒሁ ምንጫችን የገለፁትን አቅርበናል።
ይሁንና በመንግሥት በኩል ያለውን እንዲነግሩን የማይፀብሪ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሣይ መረሣ በስብሰባ ምክንያት ትናንት ባይችሉም ዛሬ ግን በአካባቢው ምን እየተካሄደ እንደሆነና ሕዝብ መሰባሰቡን ያውቁም እንደሆን ካወያያቸው አዲሱ አበበ ጋር ተነጋግረዋል፡፡
ዝርዝሩን ያዳምጡ